ከአዲስ አበባ - አሥመራ የበረራ ጉዞ ሐምሌ 17 ይጀምራል

Wednesday, 11 July 2018 12:27

 

 የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከሐምሌ 17 ቀን 2010 ዓ.ም ጀምሮ ከ20 ዓመታት በላይ ተቋርጦ የነበረው የአሥመራ የበረራ ጉዞ እንደሚጀምር አስታወቀ። በዚህ መሠረት የደርሶ መልስ ቲኬት ዋጋ ለጊዜው 8 ሺ 944 ብር መሆኑን ይፋ አድርጓል። 1 ሰዓት ከ10 ደቂቃ ገደማ በሚፈጀው የአዲስአበባ አሥመራ በረራ ዋጋ እንደየወቅቱ ሊቀያየር እንደሚችል ገልጿል።¾

News 670                                                   Shewa

 

“ለአንዲት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን

አንድ ሲኖዶስ”

በኢ/ኦ/ተ/ቤተ ክርስቲያን የመንፈሳዊ አገልግሎት ማኅበራት ኅብረት

 

በይርጋ አበበ

 

በኢ/ኦ/ተ/ቤተ ክርስቲያን የመንፈሳዊ አገልግሎት ማኅበራት ኅብረት በወቅታዊ የሲኖዶስ ድርድር ጉዳይ ላይ መግለጫ ሰጠ።

የመንፈሳዊ አገልግሎት ህብረቱ “ለአንዲት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አንድ ሲኖዶስ” በሚል ርዕስ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ፤ በኢትዮጵያ የተፈጠረው የሲኖዶስ መከፋፈል ቤተ ክርስቲያንን እና አማኞችን እንደጎዳ አስታውቋል። ህብረቱ  “ላለፉት ሁለት አስርት ዓመታት በስንዴው መካከል እንክርዳድ የሚዘራው ጠላት ዲያብሎስ የኢ/ኦ/ተ/ቤተ ክርስቲያን የአስተዳደር አንድነትን በማፋለስ፤ በአበው ሊቃነ ጳጳሳት መካከል ልዩነት በመፍጠር፤ የዶግማና ቀኖና ልዩነት ሳይኖር ሲኖዶሱን እስከ መክፈል የደረሰ አሳዛኝ ተግባር መፈፀሙ መላውን ማኀበረ ምዕመናን ሲያሳዝን የኖረ ተግባር ከመሆኑም በላይ በቀደመ ታሪኳ ታላቅ በሆነችው ቤተ ክርስቲያናችን ላይ ጥቁር ነጥብ የጣለ ድርጊት ሆኖ በትውልድ የሚታወስ ነው” ሲል አስታውቋል።

የመንፈሳዊ አገልግሎት ህብረቱ አያይዞም “በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል በተፈጠረ አለመግባባት ለ20 ዓመታት ያህል ተለያይቶ የቆየውን የሁለቱ ሀገራት ህዝቦች አንድ ለማድረግ እየተደረገ ያለውን ጉልህ እንቅስቃሴና ሐምሌ 1/2010 ዓነጥብም በአስመራ ከተማ ላይ የኤርትራዊያን ወገኖቻችን የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድን በደማቅ ሁኔታ በመቀበል ለኢትዮጵያዊያን ያላቸውን ፍቅር የገለፁበት መንገድ እጅግ ልብ የሚነካ በመሆኑ በታላቅ ትህትና ያለንን አክብሮት እንገልጻለን” ብሏል።  የሁለቱ አገራት ግንኙነት በመሪዎች ብቻ ሳይሆን ‹‹በሁለቱም ሀገር ያሉ አባቶቻችንም ሊቃነ ጳጳሳትም በሁለቱ ሀገር ሕዝቦች መካከል የተጀመረው ግንኙነት እና በሁለቱ እህት አብያተ ክርስቲያናት መካከል ያለው ግንኙነት ተጠናክሮ የቤተ ክርስቲያንን አገልግሎት በጋራ በምናካሄድበት ሁኔታ ላይ ጉልህ ድርሻ እንዲኖራቸው›› ሲል ጥሪ አቅርቧል።

ከመቶ በላይ የሚሆኑ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ማህበራት በጋራ በሰጡት መግለጫ ዘመኑ የእርቅና የይቅርታ መሆኑን ተናግረዋል። የህብረቱ ሰብሳቢ ሊቀ ትጉኃን ደረጀ ነጋሽ “መሪዎች ለእርቅ እና ለሰላም ሲዘጋጁ ከመሪው ቀድሞ የተከፈተ የህዝብ ልብ አለ” ሲሉ በህዝቡ በኩል ለሰላም የተዘጋጀ መሆኑን ተናግረዋል። ሊቀ ትጉሀን ደረጀ አያይዘውም ‹‹ዘመኑ የፍቅርና የአንድነት ነው ዘረኝነት በቃን›› ብለዋል።

ህብረቱ አክሎም “የኢትዮጵያ መንግሥትና የኢ/ኦ/ተ/ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በሊቢያ ሰማዕትነት የተቀበሉ ኢትዮጵያን እንደ ግብፅ ሰማእታት ተገቢውን ትኩረት አግኝተው አጽማቸው በሀገራቸው በክብር የሚያርፍበትና እንደ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓት ተገቢው መታሰቢያ የሚደረግበት ሁኔታ እንዲኖር አበክረን ጥሪ እያስተላለፍን በዚህ ረገድ የማኀበራት ኅብረት የድርሻውን ለመወጣት ዝግጁ መሆኑን ለመግለፅ ይወዳል” ሲል የበኩሉንም እንደሚወጣ አስታውቋል።

ህብረቱ በመጨረሻም “በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገር የሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ በቤተ ክርስቲያን ምዕመናንም ይህ የተጀመረው የእርቀ ሰላም ጥረት በምንም ምክንያት ወደኋላ እንዳይመለስ በጸሎትም በሐሳብም የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ ጥሪ እናስተላልፋለን” ብሏል።  

 

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
88 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 1050 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us