የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የልዩ ኃይል አዛዦችን አሰናበተ

Wednesday, 04 July 2018 12:46

 

የቤንሻንጉል ክልል መንግሥት በቅርቡ በተከሰተው ሁከትና ብጥብጥ ስራቸውን በአግባቡ አልመሩም ያላቸወን ሁለት የክልሉ ልዩ ኃይል አዛዦችን ከስራ አሰናብቷል እንደሁም ከፍተኛ አመራሮችን ከስራ አግዷል።

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን ትላንት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንደተናገሩት “የክልሉ አስተዳደርና ጸጥታ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ ኃላፊ አቶ ዲንሳ በየነ እና የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሸነር አብደላ ሼኸዲን ከስራቸው የታገዱ ሲሆን የክልሉ ልዩ ኃይል አዛዥ ኮማንደር ፈረደ ቦጂ እና ኮማንደር ረጅብ እስማኤል ከስራቸው እንዲሰናበቱ” ተደርጓል ብለዋል። የማስተካከያ እርምጃዎችም በቀጣይ ከክልል እስከ ቀበሌ ድረስ የሚቀጥል መሆኑን አቶ አሻሃዲሊ ሀሰን አስታውቀዋል።

እርምጃው የተወሰደው በክልሉ በማኦ እና ኮሞ ልዩ ወረዳ፣ በአሶሳ ከተማና በሸርቆሌ የተከሰተው ሁከትና ብጥብጥ ከመከሰቱ አስቀድሞ ከመከላከልና ከተከሰተ በኃላም ከማረጋጋት አኳያ የነበራቸው ሚና ዝቅተኛ በመሆኑ ሲሆን የተከሰተው ሁከትም የሰው ህይወትና ንብረት ላይ ጉዳት ከማስከተሉ አስቀድሞ መከላከል እንደሚቻል ር/መስተዳድሩ አያይዘው ገልጸዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ እንደገለጹት እስካሁን ከግጭቱ ጋር በተያያዘ ህይወታቸው ያለፉ ሰዎች ቁጥር 14 መድረሱን ገልጸው በአሁኑ ሰዓት 11 የሚሆኑ ታካሚዎች በሆስፒታል እርዳታ እየተደረገላቸው መሆኑን አሳውቀዋል።

በተፈጠው ችግርም የክልሉ መንግሥት ከፍተኛ ሀዘን የተሰማው መሆኑን በመግለጽ ህይወታቸውን ላጡ ወገኖች መጽናናትን፣ በህክምና ላይ ለሚገኙትም ፈውስን ተመኝተዋል። የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻሀድሊ ሀሰን በክልሉን መንግሥት ስም ይቅርታ ጠይቀዋል።

በመጨረሻም ጉዳት የደረሰባቸውን አካላትን ለመለየት ኮሚቴ ተዋቅሮ እየተሰራ መሆኑን ገልጸው ለተጎዱ ዜጎች የክልሉ መንግሥት ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልጸዋል።

የምርምራው ስራም ተጠናክሮ የሚቀጥል ሲሆን በሁከትና ብጥብጡ ተሳታፊ ሆኖ የተገኘ ማንኛውም አካል ለህግ እንደሚቀርብ አስታውቀዋል።¾

ይምረጡ
(1 ሰው መርጠዋል)
256 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 1020 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us