የሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ኩባንያዎች አመራሮችና ሠራተኞች “ሼህ ሙሐመድ ይፈቱ” የሚል ዘመቻ በይፋ ጀመሩ

Wednesday, 27 June 2018 12:54

 

የሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ኩባንያዎች ቺፍ ኤግዚኪዩቲቭ ኦፊሰር/ፕሬዚዳንት ዶ/ር አረጋ ይርዳው ሳዑዲ አረቢያ በእስር ላይ የሚገኙት የሚድሮክ ኢትዮጵያ ሊቀመንበር እና የክብር ዶ/ር ሼህ ሙሐመድ ሁሴን አሊ አል አሙዲንከእሥር ለማስፈታት መንግሥት የሚያደርገውን ጥረት አድንቀው ይህ ዲፕሎማሲያዊ ጥረት እንዲቀጥል ጠየቁ።

ዶ/ር አረጋ ይህንን ጥያቄ ያቀረቡት ሰኔ 14 ቀን 2010 ዓ.ም በመቻሬ ኮርፖሬት ሴንተር መቻሬ ሜዳ የቴክኖሎጂ ግሩፑ 26 ኩባንያዎች አመራሮችና ሠራተኞች በተገኙበት ስብሰባ ላይ ባደረጉት ንግግር ነው። ዶ/ር አረጋ በዚሁ ንግግራቸው ሼህ ሙሐመድ ታሰሩ ከተባሉበት ዕለት ጀምሮ ከቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝጋር በጋራ በመሆን ሼህ ሙሐመድን ለማስፈታት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የተደረገ ቢሆንም በአገራችንም ሆነ በሳዑዲ አረቢያ መንግሥት ተከስተው በነበሩት ለውጦች ምክንያት ጉዳዩ መፍትሔ ሳያገኝ ቆይቷል።

ነገር ግን አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ሥራ በጀመሩ በአጭር ጊዜ ከሳዑዲ አረቢያ መንግስት ጋር በመነጋገር ሊቀመንበራችን እንደሚፈቱ የሰጡን ተስፋ በእጅጉ ሊያስደንቅና ሊያስመሰግናቸው ይገባል፤ እኛም የኩባንያዎቻችን አለኝታ የሆኑትን የክብር ዶ/ር ሼህ ሙሐመድ ሁሴን አሊ አል አሙዲን ለመቀበል በጉጉት እየጠበቅን እንገኛለን። ዲፕሎማሲ ግንኙነት ከፈጠርንበት ቀን ጀምሮ ይህንን አሁን ያደረጋችሁትን ቲሸርት በአስቸኳይ በማሠራት ሊቀመንበራችንን አንረሳም፣ አሉ እየመሩን ነው፣ ኩባንያዎቹን በአደራ እንደተረከብን በአደራ ማስረከብ አለብን፣ በአስችኳይ ይፈቱልን በማለት ዝግጅት ጀምረን የነበረ ቢሆንም በወቅቱ አገሪቱ ከነበረችበት አኳያ ሁኔታዎች ሳይፈቅዱልን ቆይተናል። በርካታ አጋር ድርጅቶች እንዲሁም ያገባናል ባይ ግለሠቦችን ጨምሮ የሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ሠራተኞች በአካል፣ በግጥም፣ በደብዳቤ ለሊቀመንበራችን ምን እናድርግ በማለት ላለፉት ሰባት ወራት ያደረጋችሁትን ጥረት አደንቃለሁ። በአገሪቱ የነበረውን ነባራዊ ሁኔታ እና ህጉን በማክበርም ጥያቄያችንን በድምፅ አልባ የውስጥ የይፈቱልን ግንኙነት ስናደርግ ቆይቷል።

ጥያቄያችን ተገቢ ቢሆንም በወቅቱ ተግባራዊ ለማድረግ አልተቻለም ብለዋል። የዕለቱንም ስብሰባ ለማድረግ ከተገቢው አካል ፈቃድ ተገኝቶ የተደረገ መሆኑንም ተናግረዋል። በማያያዝም መንግሥት በገባው ቃል መሰረት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቱን በማፋጠን የገባውን ቃል እንዲያከብርልን ጥያቄያችንን እንገፋበታለን ብለዋል።

በተጨማሪም የሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ሠራተኞች በየኩባንያዎች ሼህ ሙሐመድን ከእስር እስኪፈቱ ድረስ የክብር ዶ/ር ሼህ ሙሐመድ የምናስብበት ቀን በየሳምንቱ ማክሰኞ ዕለት ከምሳ ሰዓት በፊት እንዲሆን መወሰኑን ዶ/ር አረጋ ገልጸዋል። በዚሁ መሠረት ማክሰኞ የሁሉም ኩባንያዎች አመራርና ሠራተኞች የሚሰጠውን የማስታወሻ ቲሸርት በመልበስ በየኩባንያዎቻቸው ሁልጊዜ በመሰብሰብ ማሰብ ይጠበቅብናል ብለዋል።

በመጨረሻም ሼህ ሙሐመድ ሁሴንን ሥራችንን እየሠራን እንድናስባቸው አሳስባለሁ። ይህንን የምናደርገው ለእርሳቸው፣ ለህሊናችንና ለአገራችን ሲባል ነው ያሉት ዶ/ር አረጋ ዛሬም በተቀናጀ እና ሕግን ባከበረ መልኩ እንዲፈቱ የምናደርገውን ጥረት አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል።¾

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
266 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 1036 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us