የዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ ዓመታዊ የጥናትና ምርምር ኮንፈረንስ ተከናወነ

Wednesday, 27 June 2018 12:46

 

ዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ 17ኛውን ዓመታዊ የጥናትና ምርምር ኮንፈረንስ ዓርብ ሰኔ 15 ቀን 2010 ዓ.ም በመቻሬ ሜዳ አካሄደ።

የዪኒቲ ዩኒቨርሲቲ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚደንት ዶ/ር ብርሃኑ ሲሳይ በኮንፈረንሱ መክፈቻ ሥነሥርዓት ላይ ባደረጉት ንግግር በዕለቱ ከመንግሥትና ከግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተመራማሪዎች የቀረቡ 22 ጥናታዊ ጹሑፎች መመረጣቸውን ጠቅሰው ጥናቶቹ ለዘርፉ ዕድገት የራሳቸውን አዎንታዊ አስተዋጽኦ እንደሚኖራቸው እምነታቸውን ገልጸዋል።

በዕለቱ የቀረቡት 22 ጥናታዊ ጹሑፎች በአምስት ክፍሎች ማለትም በትምህርት፣ በጤና፣ በእርሻና አየር ንብረት ለውጥ፣ በቢዝነስና እና ኢንዱስትሪ፣ በሁለገብ ጥናቶች ተከፋፍለው በአራት አዳራሾች እንዲካሄዱ መደረጉ ታውቋል። የኮንፈረንሱ ታዳሚዎችም የሚፈልጉት አዳራሽ በመሰየም ጥናቶቹ ከቀረቡ በኋላ ተወያይተውባቸዋል።

ኮንፈረሰንሱ በሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ቺፍ ኤግዚኪዩቲቭ ኦፊሰር እና የዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት ዶ/ር አረጋ ይርዳው በተገኙበት ተጠናቋል።¾

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
115 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 1063 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us