በውጭ ምንዛሪ እጥረት ችግር የተፈተነው ሀይሌ ሪዞርት አምስተኛ ሆቴሉን በአርባ ምንጭ ገነባ

Wednesday, 13 June 2018 12:52

 

በይርጋ አበበ

ኃይሌ እና ዓለም ኢንተርናሽናል አምስተኛ ሆቴሉን በአርባ ምንጭ ከተማ ገንብቶ ማጠናቀቁን ገለፀ።

የኃይሌ እና ዓለም ኢንተርናሽናል ሥራ አስኪያጅ አትሌት ኃይሌ ገብረስላሴ እንደገለፀው ሆቴሉን ገንብቶ ለማጠናቀቅ ከአንድ ዓመት ተኩል ባልበለጠ ጊዜ ማጠናቀቁን ተናግሯል።

በግንባታው ወቅት ስለገጠመው ችግር ከጋዜጠኞች ለቀረበለት ጥያቄ “የውጭ ምንዛሪ አሳሳቢ ሆኖብን ነበር። በዚህ የተነሳም አንዳንድ የፈርኒቸር ምርቶችን በከፍተኛ ጥራት አገር ውስጥ ለማስመረት ለመሙላት ሞክረናል” ብሏል።

ሻለቃ ኃይሌ አያይዘው በአገሪቱ ተጥሎ የቆየው አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የሆቴል ቢዝነሱን በጣም ጎድቶባቸው እንደቆየ ገልጿል። “እንዲያውም አንዳንድ ጊዜ የሰራተኛ ደመወዝ ከግል በማውጣት በመሸፈን ተገድደን ነበር” ሲሉ ተናግሯል።

በአርባ ምንጭ የተገነባው አምስተኛው ኃይሌ ሪዞርት 375 ሚሊዮን ብር ወጭ የፈጀ ሲሆን 110 የእንግዳ ክፍሎች አሉት።

ከአርባ ምንጭ በተጨማሪም በቅርቡ በአዲስ አበባ፣ ደብረብርሃን፣ አዳማ እና ኮንሶ ተመሳሳይ ሆቴሎችን ለመገንባት ወደ ሥራ መግባቱን አትሌት ኃይሌ ገ/ሥላሴ ተናግሯል።

“ውድድራችን በአገር ውስጥ ብቻ ሳይገታ ዓለም አቀፍ ነው” ያለው፤ አትሌት ኃይሌ በአርባ ምንጭ ሆቴል ግንባታ ከሂደቱ ጀምሮ የመንግስት ቢሮክሲ እንደሌሎች አካባቢዎች የተንዛዛ አለመሆኑን በአድናቆት ገልፆታል። በዚህም የዞኑንና የአካባቢውን አስተዳዳሪዎች አመስግኗል።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
1059 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 121 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us