ሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ የብዙነሽ በቀለን የመታሰቢያ ሐውልት አደሰ

Wednesday, 09 May 2018 13:13

 

"እናቱን የማይወድ ሰው አለ ቢሉኝ

ሰው ነው አልለውም አውሬ ነው ባይ ነኝ።"

የአንጋፋዋ ድምጻዊት ብዙነሽ በቀለ ዘመን አይሽሬ እንጉርጉሮ ነው። ይህን ዘፈን የሰማ ሁሉ የእናቱ ትዝታና ፍቅር በውስጡ መቀስቀሱና እናቱን ማሰቡ አይቀሬ ነው።

አምና በዚህ ወቅት በሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ መቻሬ ኮርፖሬት ሴንተር "የእናት ቀን" ሲከበር ቺፍ ኤግዚኪዩቲቭ ኦፊሰር ዶ/ር አረጋ ይርዳው ድምጻዊት ብዙነሽ በቀለን በተወዳጁ የእናት ዜማዋ አስታወሷት። ማስታወስ ብቻም አይደለም፤ ለዚህ ዘመን አይሽሬ ዘፈንዋ መታሰቢያ እንዲሆን ሐውልትዋን ለማደስ ቃል ገቡ።

እነሆ ዓመቱን ቆጥሮ በትላንትናው ዕለት (በእናት ቀን ዋዜማ) የአርቲስትዋ ቤተሰቦች፣ ወዳጆች አድናቂዎች በተገኙበት በቅዱስ ዮሴፍ ቤተክርስቲያን ታድሶ የቆመው የብዙነሽ በቀለ ሐውልት ለምረቃ በቅቷል።

በሥነሥርዓቱ ላይ ሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕን በመወከል በሥፍራው የተገኙት አቶ ጌታነህ ምትኩ ባደረጉት አጭር ንግግር ዶ/ር አረጋ የእናት ቀንን ማክበር በቴክኖሎጂ ግሩፑ እንዲጀመር ማድረጋቸውና የብዙነሽ በቀለ ሐውልት እንዲታደስ መወሰናቸው ለሴቶችና ለእናቶች ያላቸውን ክብር የሚገልጽ ነው ብለዋል። የሐውልቱን እድሳት የቴክኖሎጂ ግሩፕ አባል ኩባንያ በሆነው ሁዳ ሪልስቴት መከናወኑን ተናግረዋል።

አቶ መሐመድ ኢንድሪስ የብዙነሽ በቀለ የቀድሞ ባለቤት በበኩላቸው በሐውልቱ አሠራር በእጅጉ መርካታቸውን በመግለጽ ሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ በሐውልቷ ላይ ሕዝባዊ አሻራውን አኑሯል ሲሉ ተናግረዋል። አያይዘውም እናት በሕይወት ሩጫ ላይ የሶስት ሜዳሊያዎች ባለቤት ናት፣ ወርቁ፣ ብሩም ነሐሱም የእናት ነው፣ ዋጋዋ ሊከፈል አይቻልምና ብለዋል።

ይምረጡ
(1 ሰው መርጠዋል)
716 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 1032 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us