ከአገር ሊወጡ ሲሉ በቁጥጥር ስር የዋሉ ጥንታዊ ቅርሶች ለባለስልጣኑ ተመለሱ

Wednesday, 11 October 2017 12:37

የባህል አልባሳትና ቅርሳቅርስ መሸጫ መደብሮች የአገሪቱ ውድ ቅርሶችና ጌጣጌጦች በድብቅ የሚሸጡባቸው እየሆኑ መምጣታቸው ተጠቆመ። ትናንት ማክሰኞ (መስከረም 30 ቀን 2010ዓ.ም) የፌዴራል ፖሊስ ለቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን አንድ መቶ የሚደርሱ ጥንታዊ የብራና መጽሀፍትን አስረክቧል። እዚህ ጥንታዊ መፅሐፍት በህገወጥ መንገድ ከሀገር ሊወጡ ሲሉ በቁጥጥር ስር የዋሉ መሆናቸውም ተገልጿል። ቅርሶቹ ከ2007 እስከ 2009 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ በሶስት ግለሰቦች እጅ የነበሩና ተሸጠው ወደውጪ ሊወጡ ሲሉ በፌዴራል ፖሊስ ክትትል የተያዙ መሆናቸውም ታውቋል።

 

በፖሊስ ምርመራና ክትትል መነሻነት ከአንድ ግለሰብ ላይ 65 የሚሆኑ ጥንታዊ የብራና መፅሀፍትና የዱር እንስሳት የጌጣጌጥ ውጤቶች በቁጥጥር ስር ውለዋል። ከኢትዮጵያ ለመውጣት ሲል በቁጥጥር ስር የዋሉ በስም ያልተጠቀሰው ቻይናዊ በእጁ አጥልቆት የነበረውን “አንባር” ከየት እንዳመጣው ፖሊስ ባደረገው ማጣራትን ተከትሎ በተደረገ ምርመራ ቅርሶቹ መገኘታቸውንም ለማወቅ ተችሏል። በቁጥጥር ስር የዋለውን ቻይናዊ ተከትሎ ሽያጩን የፈፀሙለት ግለሰቦች መደብሮች ድንገተኛ ፍተሻ በማካሄድ ከሌሎች ቅርሶች ጋር እነዚህ አገር በቀል ውድ ቅርሶች ተይዘዋል ተብሏል።


በቅርሳቅርስና የባህል አልባሳት መደብሮቹ ውስጥ የተገኙት እነዚህ ጥናታዊ የብራና መፅሀፍትና ከእንስሳት የተሰሩ ጌጣጌጦች ጥንታዊ ቅርስ እንዳልሆኑና የእንስሳት ምርቶችም አለመሆናቸው ቢነገርም በምርመራ በመረጋገጣቸው ፌዴራል ፖሊስ በቁጥጥር ስር አውሏቸዋል።


ጥንታዊ ቅርሶች በግለሰቦች፣ በሃይማኖት ተቋማትና በመንግስት እጅ የሚገኙ ቢሆንም፤ ታሪካዊ ፋይዳቸው ግን አገራዊ ስለሆነ በምንም አይነት መልኩ ህጋዊ ባልሆነ መንገድ ከሀገር መውጣት እንደሌለባቸው ተጠቁሞ፣ ህብረተሰቡም መሰል እንቅስቃሴዎችን በመከላከል ትብብሩን እንዲያሳይ ተጠይቋል።


ከአንድ መቶ በላይ የሚሆኑት እነዚህ ቅርሶች በፌዴራል ፖሊስ በኩል ለቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን ሲመለሱ የመጀመሪያ መሆኗቸውን በመጥቀስ፤ በቀጣይም የፍርድ ሂደታቸው ሲጠናቀቅ ወደባለስልጣኑ ተመላሽ የሚሆኑ በርካታ ጥናታዊ ቅርሶች መኖራቸውን በርክክቡ ወቅት ተጠቅሷል። ከዚህም በፊት ከፌዴራል ፖሊስ ባለፈ በፌዴራሉ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን በኩል ተመላሽ የሆኑ ቅርሶች እንዳሉ ለትውስታ ተነግሯል።

ይምረጡ
(2 ሰዎች መርጠዋል)
749 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 1039 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us