ዩኒቲ ዩኒቨርስቲ 12ኛውን የኪነ ህንፃ ኤግዚብሽን አካሄደ

Wednesday, 11 October 2017 12:44

 

በዩኒቲ ዩኒቨርስቲ አዘጋጅነት በየዓመቱ የሚካሄደው የኪነ ህንፃ አውደ ርዕይ በዚህ ዓመትም ከመስከረም 25 ቀን እስከ መስከረም 28 ቀን 2010 ዓ.ም ድረስ በብሄራዊ ቴአትር ተካሂዷል። በዚሁ የኪነ ህንፃ አውደ ርዕይ ላይ የዩኒቲ የኒቨርስቲ የአርክቴክቸር እና የከተማ ፕላን ክፍል ተማሪዎች የተለያዩ የፈጠራ ሥራዎቻቸውን ለዕይታ አቅርበዋል። ኤግዚብሽኑ ለ12ኛ ጊዜ የተካሄደ ሲሆን በርካታ ጎብኚዎችም በቦታው በመገኘት ተመልክተውታል። በመክፈቻው ዕለት አጠር ያለ ማብራሪያ የሰጡት የሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ሲኢኦና የዩኒቲ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር አረጋ ይርዳው፤ መሰል ኤግዚብሽኖች፤ ተማሪዎች ስራዎቻቸውን ለህዝብ እይታ እንዲያቀርቡ የተሻለ መድረክ መሆኑን ገልፀው፤ የማህበረሰቡን የኪነ ህንፃ ግንዛቤም ለማሳደግ ቀላል የማይባል አስተዋፅኦ ያለው መሆኑን አመልክተዋል።

 

በዩኒቲ ዩኒቨርስቲ የአርክቴክቸራል ዲፓርትመንት መመህር የሆኑት ቴዎድሮስ ገብረፃድቅ ኤግዚብሽኑ ከመጀመሪያ ዓመት ጀምሮ እስከ አምስተኛ ዓመት ድረስ ያሉ ተማሪዎች ስራዎቻቸውን ለህዝብ ዕይታ የሚያቀርቡበት መድረክ መሆኑን ገልፀውልናል። ይህም ሁኔታ አንድ ተማሪ ከየት ጀምሮ የት ደረሰ የሚለውንም ሂደት ለማሳየት ፕሮጀክቶቹ ሰፊ ዕገዛ የሚያደርጉ መሆኑን መምህሩ አመልክተዋል።

 

 በኤግዚብሽኑ ላይ የሚቀርቡት ሥራዎች የሁሉም ተማሪዎች ሥራ ሳይሆኑ የተወሰኑ ተማሪዎች ሥራ መሆኑ ታውቋል። ቦታው የተማሪዎቹን ሥራ ለማቅረብ እንደዚሁም ጎብኚዎችን በበቂ ሁኔታ ለማስተናገድ ውስንነት ይታይበታል። ቦታው የጠበበ መሆኑን ያመለከቱት ዶክተር አረጋ፤ ችግሩ ቢታወቅም ቦታውን ሰው የለመደው በመሆኑና ለጎብኚዎችም በቀላሉ ተደራሽ በመሆኑ ዝግጅቱ በተለመደው ስፍራ እንዲካሄድ የተደረገ መሆኑን ገልፀዋል።

 

በኤግዚብሽኑ ላይ የኤግዚብሽን ማዕከል፣ የመኖሪያ አፓርትመንቶችና የመሳሰሉት ሥራዎች የቀረቡ ሲሆን አንድ የግንባታ ሥራ ከአካባቢው ጋር በምን መልኩ ተጣጥሞ መሰራት እንዳለበት በኤግዚብሽኑ ላይ በቀረቡት ሥራዎች ላይ ጎልቶ ታይቷል።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
254 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 1048 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us