ሼክ ሙሐመድ የቴክኖሎጂ ግሩፑ የሠራተኞች ስፖርታዊ ውድድር ሌሎችንም ኩባንያዎች አካቶ እንደሚቀጥል አረጋገጡ

Wednesday, 25 May 2016 12:56

“ስፖርታዊ ውድድሩ የሠራተኛውን ህብረት አጠናክሯል”

                       ዶ/ር አረጋ ይርዳው

 

 

በሚድሮክ ኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ግሩፕ 24 እህትማማች ኩባንያዎችና 11 ተጋባዥ ተቋማት መካከል ከጥር 22 ቀን 2008 ዓ.ም ጀምሮ በተለያዩ የስፖርት አይነቶች ሲካሄድ የቆየው ዓመታዊ የስፖርት ውድድር በመቻሬ ሜዳ ኮርፖሬት ሴንተር ግቢ እሁድ ግንቦት 14 ቀን 2008 ዓ.ም  በተጠናቀቀበት ሥነሥርዓት ላይ የተገኙት የሚድሮክ ሊቀመንበርና ባለቤት የክብር ዶ/ር ሼክ ሙሐመድ ሁሴን ዓሊ አልአሙዲ ስፖርታዊ ውድድሩ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋገጡ።

ሼክ ሙሐመድ በሠራተኞቹ ስፖርታዊ ውድድር የመዝጊያ ሥነሥርዓት ላይ በክብር እንግድነት የተገኙ ሲሆን በዚህ ወቅት ከጋዜጠኞች ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች መልስ ሰጥተዋል። ዶ/ር አረጋ ይርዳው ሠራተኛው እንዲሰባሰብ፣ ልጆቹን ቤተሰቡን ይዞ መጥቶ በስፖርት ራሱን እንዲያዝናና፣ እንዲወዳደር ማድረጉ አንድነት እንዲኖር የሰጠው ጠቀሜታ ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል። ስፖርታዊ ውድድሩ ለሠራተኛውም ለቤተሰቡም፣ ለኩባንያዎቹም ይጠቅማል ያሉት ሼክ ሙሐመድ ወደፊት ሁሉም ኩባንያዎች እንዲሰባሰቡ እንደሚደረግ ቃል ገብተዋል።

የሚድሮክ ኢትዮጵያ ቺፍ ኤግዚኪዩቲቭ ኦፊሰር ዶ/ር አረጋ ይርዳው በበዓሉ መዝጊያ ወቅት ባደረጉት ንግግር ለአምስት ወራት ድምቀቱን ጠብቆ ሲካሄድ በቆየው ዓመታዊ የስፖርት ውድድር መዝጊያ ላይ ለተገኛችሁ የተለያዩ ኩባንያዎችና ተቋማት ቤተሰቦች፣ እንዲሁም በስፖርታዊ ጨዋነት በመካፈል ለዛሬዋ ቀን ለበቃችሁ የውድድሩ ተሳታፊዎች እና እንግዶቻችን፣ እንኳን ደህና መጣችሁ ካሉ በኃላ በሚድሮክ ኢትዮጵያ ሊቀመንበርና ባለሀብት ሼህ መሐመድ ሁሴን አሊ አል አሙዲ በባለቤትነት የሚመሩቸውን ኩባንያዎች ሠራተኞች የእርስ በእርስ ግንኙነት ለማጠናከር ለ13ኛ ጊዜ ሲካሄድ የነበረው ዓመታዊ የስፖርት ውድድር ውጤታማና የታለመለትን ግብ የመታ በመሆኑ ለወደፊቱም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስረድተዋል።

ዶ/ር አረጋ ለጋጠኞች በሰጡት ቃለምልልስ ስፖርታዊ ውድድሩ 13ኛ ዓመቱን መያዙን በማስታወስ ዓላማው በሠራተኛው መካከል ሕብረት እንዲኖር፣ ሠራተኛው ጤናውን እንዲጠብቅ፣ ቤተሰብ እንዲተዋወቅ፣ ልጆች ይህንን እያዩ እንዲድጉ ነው። ስፖርት ለማኔጅምንት ትልቅ መሣሪያ ነው። በእስካሁኑ እንቅስቃሴ ብዙ ለውቶችን አይተንበታል ብለዋል። በቅርቡም ለሠራተኞች ጥቅም የሚሰጥ የስፖርት ጅምናዚየም በመቻሬ ሜዳ ለማስገንባት ማቀዳቸውንም ዶ/ር አረጋ ይፋ አድርገዋል።

በሚድሮክ ኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ሲኢኦ ቢሮ አዘጋጅነት ሲካሄድ በቆየው በዚሁ 13ኛው ዓመታዊ የስፖርት ውድድር ላይ ቴክ ሳር ቤት፣ቴክ አቃቂ፣ ቴክ መገናኛ፣ ቴክ ሰሚት፣ እንዲሁም ከተጋባዥ ኩባንያዎችና ተቋማት፤ፖልሪያስ፣ዳሽን ባንክ፣ኢትዮ ቴሌኮም (ደቡብ ምዕራብ ቀጠና ቅርንጫፍ) ፣ናሽናል ሞርስ፣ሞሐ ለስላሳ መጠጥ ኢንዱስትሪ፣አዲስ ኢንተርናሽናል ኬተሪንግ፣ኒያላ ኢንሹራንስ፣ሆራይዞን አዲስ ጎማ፣ኢኳቶሪያል ቢዝነስ ግሩፕ፣ኢትዮ ሌዘር ኢንዱስትሪ እና ሜፖ ኮንስትራክሽን እና ማኔጅመንት ሰርቪስ ተካፋይ ነበሩ።

በዚሁ ዓመታዊ ስፖርት ውድድር፣ እግር ኳስ፣ መረብ ኳስ፣ ገመድ ጉተታ፣ ሜዳ ቴኒስ፣ ሩጫ፣ ዱላ ቅብብል፣ የጠረጴዛ ቴኒስ፣ ቼዝ፣ ዳማና ሌሎችም ልዩ ልዩ የስፖርት ውድድሮች ተካሂደዋል። በአጠቃላይ በውድድሩ የተሳተፉት ስፖርተኞች ብዛት 551 ሲሆን ከዚህ ውስጥ 411 ወንዶች 140 ደግሞ ሴቶች ናቸው።

በስፖርት በዓሉ መዝጊያ ላይ የሚድሮክ ኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ኩባንያዎች ከፍተኛ የሥራ አመራር አባላት፣ ሠራተኞና ቤተሰቦቻቸው፣ የተጋባዥ ኩባንያዎች እና ተቋማት ተወካዮች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

በሚድሮክ ኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ሥር የሚገኙ ኩባንያዎች ብዛት 24 የደረሰ ሲሆን ሼክ ሙሐመድ በኢትዮጵያ ያላቸው የተለያዩ ኩባንያዎች ጠቅላላ ብዛት ከ70 በላይ መሆኑ ታውቋል። በሚድሮክ ኢትዮጵያ ቺፍ ኤግዚኪዩቲቭ ኦፊሰር ዶ/ር አረጋ ይርዳው አማካይነት የዛሬ 13 ዓመት የተጠነሰሰው ዓመታዊ የሠራተኞች ስፖርታዊ ውድድር ከቀጣይ ዓመት ጀምሮ ሼክ ሙሐመድ በገቡት ቃል መሠረት በርካታ ኩባንያዎች ይሳተፉበታል ተብሎ ይጠበቃል።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
631 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 1052 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us