የሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ኩባንያዎች እና ተጋባዥ ተቋማት ዓመታዊ የስፖርት ውድድር

Wednesday, 08 March 2017 12:18

በሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ኩባንያዎችና ተጋባዥ ተቋማት መካከል የሚካሄደው ዓመታዊ የስፖርት ውድድር የካቲት 26 ቀን 2009 ዓ.ም በመቻሬ ሜዳ ኮርፖሬት ሴንተር ግቢ ተጀመረ።

የሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ቺፍ ኤግዚኪዩቲቭ ኦፊሰር ዶ/ር አረጋ ይርዳው በዚህ ዓመታዊ የስፖርት ውድድር መክፈቻ በዓል ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር፤ የሚድሮክ ኢትዮጵያ ሊቀመንበርና ባለሀብት የክብር ዶ/ር ሼህ ሙሐመድ ሁሴን አሊ አል-አሙዲ በባለቤትነት የሚመሩዋቸውን ኩባንያዎች ሠራተኞች የእርስ በርስ ግንኙነት ለማጎልበት፣ ጤናማ የኢንዱስትሪ ሠላም ለማስፈን፣ በኩባንያዎቹ መካከል የወዳጅነት መንፈስን ለማጠናከር በየዓመቱ በሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ አዘጋጅነት ለ14ኛ ጊዜ ስፖርታዊ ውድድሩ እንደሚካሄድ አስታውሰዋል።

ዶ/ር አረጋ አያይዘውም የሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ 25 ኩባንያዎችን በአራት የቴክ ምድብ በመመደብ እንዲሁም 11 ሌሎች ተጋባዥ እህት ኩባንያዎች እና ተቋማት በተለያዩ የስፖርት ዓይነቶች ለመወዳደር ዝግጅታቸውን ማጠናቀቃቸውን በማብሰር ስፖርተኞቹን እንኳን ደህና መጣችሁ ብለዋል። 

የክብር ዶ/ር ሼህ ሙሐመድ ሑሴን አሊ አልአሙዲ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ወደ 74 ኩባንያዎች እንዳሉዋቸው ያስታወሱት ዶ/ር አረጋ በእንዲህ ዓይነቱ ስፖርታዊ መድረክ ሁሉም ኩባንያዎች ተሳታፊ የሚሆኑበት ጊዜ ሩቅ እንደማይሆን ተናግረዋል።

«የእኛ ዋንኛ ዓላማ ፕሮፌሽናል ስፖርተኛ ማፍራት ሳይሆን ስፖርታዊ ውድድሩ ለጤንነት፣ ለወዳጅነት፣ ለፍቅር እና ምርታማነትን ለማሳደግ እንዲያገለግለን ነው» ብለዋል።

በስፖርት ውድድሩ መክፈቻ ዕለት ከሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ አራት ምድቦች መካከል የሆኑት የቴክ መገናኛ እና የቴክ አቃቂ የእግር ኳስ ቡድኖች ግጥሚያቸውን አድርገዋል።

ባለፈው እሁድ  የተጀመረው ይኼው ዓመታዊ የስፖርት ውድድር፤ እግር ኳስ፣ መረብ ከስ፣ ጠረጴዛ ቴኒስ፣ ገመድ ጉተታ፣ ሜዳ ቴኒስ፣ ሩጫ፣ ድላ ቅብብል፣ ቼዝ፣ ዳማና ሌሎች ልዩ ልዩ የስፖርት ዓይነቶች የሚካሄዱበት እንደሚሆን ለማወቅ ተችሏል።

በሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ሲኢኮ (CEO) ቢሮ አዘጋጅነት በሚካሄደው ዓመታዊው የወዳጅነት የስፖርት ውድድር የቴክኖሎጂ ግሩፕ ኩባንያዎች የሆኑት፤ ቴክ ሣር ቤት ፣ ቴክ አቃቂ፣ ቴክ መገናኛ፣ ቴክ ሰሚት እንዲሁም አስራ አንድ ተጋባዥ ኩባንያዎች እና ተቋማት ማለትም፤ ፖልሪዬስ፣ ዳሸን ባንክ፣ ኢትዮ ቴሌኮም (ደቡብ መዕራብ ቀጠና ቅርንጫፍ)፣ ናሽናል ሞተርስ፣ ሞሐ ለስላሳ መጠጥ ኢንዱስትሪ (የንፋስ ስልክ ፋብሪካ)፣ አዲስ ኢንተርናሽናል ኬተሪንግ፣ ኒያላ ኢንሹራንስ፣ ሆራይዘን አዲስ ጎማ፣ ኢኳቶሪያል ቢዝነስ ግሩፕ፣ ኢትዮ ሌዘር ኢንዱስትሪ እና ሜፖ ኮንስትራክቲንግ እና ማኔጅመንት ሰርቪስ ተካፋይ ይሆናሉ።

በስፖርት በዓሉ መክፈቻ ላይ የሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ኩባንያዎች ከፍተኛ የሥራ አመራር አባላት፣ ሠራተኞችና ብተሰቦቻቸው፣ የተጋባዥ ኩባንያዎች እና ተቋማት ተወካዮች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።   

ስፖርታዊ ውድድሩ ከሶስት ወራት በኋላ የማጠናቀቂያ ውድድሩ በወልዲያ ከተማ ተገንብቶ በቅርቡ በተመረቀው የሙሐመድ ሁሴን አሊ አልአሙዲ ስታዲየም እንደሚከናወን ዶ/ር አረጋ ፍንጭ ሰጥተዋል።

በዕለቱም በሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ስር የሚገኙ 25 ኩባንያዎች ለህዳሴ ግድብ ግንባታ የሚውል የሶስት ሚሊየን ብር የቦንድ ግዥ እንደሚፈጽሙ ዶ/ር አረጋ ይፋ አድርገዋል።¾

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
443 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 106 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us