በወወክማ የቦርድ አባላት ምርጫ የተፈፀመውን የሕግ ጥሰት የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት ኤጀንሲ በሕግ በተሰጠው ሥልጣን የማስተካከያ ርምጃ አለመውሰዱ ለምን ይሆን?

Wednesday, 30 August 2017 13:25

 

ከብርሃኑ አክሊሉ

የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት ኤጀንሲ ለወወክማ የቦርድ አባላት ምርጫ ዕውቅና መስጠቱ አወዛገበ በሚል ርዕስ በጋዜጣው ላይ የወጣውን ዘገባ አንብቤአለሁ።

ወወክማ በደርግ ዘመነ መንግሥት እስከተዘጋበት 1968 ዓ ም ድረስ በመላው ሃገሪቱ ለወጣቶችና ለየማህበረሰቡ ይሰጥ በነበራቸው አገልግሎቶችና ፕሮግራሞች እጅግ የሚወደድ ማሕበር ነበር። ይህ ማህበር ወደ ቀድሞው ዝናው እንዲመለስ ከሚጓጉ በርካታ የቀድሞ አባላት መካከሉ አንዱ ነኝ። ካለፈው የካቲት ወር ጀምሮ 6 ወራትን በሚፈጁ ልዩ ልዩ ክንውኖች  የወወክማን 70 ኛ ዓመት ክብረ በዓል እንዲያዘጋጁ ከተቋቋሙት ኮሚቴዎች በአንዱ የበጎ ፈቃድ  አገልግሎት እሰጥ ስለነበር ስለተፈፀመው የሕግ ጥሰት የማወቁ ዕድል አለኝ።

የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት ኤጀንሲ በቀረበበት ቅሬታ ላይ ምላሽ አልሰጠም። ስለሆነም በቦርድ አባላት ምርጫው ላይ ከሁለቱም ወገኖች በተሰነዘሩት ሃሳቦች ላኤጀንሲው ዝምታን መምረጡ የቦርድ አባላት ምርጫው ከማሕበሩ መተዳደሪያ ደንብም ሆነ በአዋጅ ከተደነገገው ውጭ የተፈፀመ መሆኑን የሚያጎላ ከመሆኑም በላይ ኤጀንሲውም በአዋጅ በግልጽ ተደንግገው በተሰጡት ሥልጣኖች ተፈጽሟል የተባለውን ሥህተት በወቅቱ እንዲታረም ካላደረገ የማሕበሩ ህልውና አደጋ ላይ እንደሚወድቅ ካለኝ ሥጋት አኳያ ይህን የግል አስተያየት ለመስጠት ተገድጃለሁ።

1.  የወወክማን 70 ኛ ዓመት ክብረ በዓል የመክፈቻ ሥነ ሥርኣት ቀን 2009 በግዮን ሆቴል በተካሄደበት ዕለት የማህበሩ ጠቅላላ ጉባኤ ከቀናት በኋላ ቀን 2009 እንደሚካሄድና የቦርድ አባላት ምርጫም እንደሚደረግ በጭምጭምታ ደረጃ ሰማን። በደንቡ መሠረት የመወያያ አጀንዳውን ዝርዝር የያዘ የጥሪ ደብዳቤ ለጉባኤ አባላት ተላልፏል ወይ ብለን ስናጣራ በሞባይል SMS እና በE-mail ለአንዳንድ ጥቂት አባላት ብቻ መልዕክት መተላለፉን ለመረዳት ችለናል።

2.  በ2009 ዓ.ም በማህበሩ ጽቤትተደረገበተባለውስብሰባምልአተጉባኤመሟላቱ በቅድሚያ ሳይረጋገጥና የማህበራት ኤጅንሲ ተወካይም ባልተገኘበት እንዲሁም ድምጽ የመስጠት መብት ሳይኖራቸው በተመልካችነት ብቻ በጉባኤው መሳተፍ የሚችሉ የየቅርንጫፍ ማህበራት ተቀጣሪ ጸሀፊዎች በአብዛኛው በተገኙበት ጠቅላላ ጉባኤ ለማድረግ አይቻልም። ደንቡን ተከትሎ በማይካሄድ ስብሰባ ላይ አንካፈልም ያሉ በርካታ አባላት ስብሰባውን አቋርጠው ወጥተዋል። የነባሩ ቦርድ አባላትም የስብሰባው አካሄድ ፈሩን ለቋል ይህ አይነት የሕግ ጥሰት ባለበት ሁኔታ ስብሰባው ሊቀጥል አይገባውም ሲሉ ተቃውሞ በማቅረብ በተመሳሳይ ሁኔታ ስብሰባውን አቋርጠው ወጥተዋል።

3.  ይሁንእንጂየጠቅላላጉባኤአባልያልሆኑሰዎችናተቀጣሪጸሃፊዎችን ጨምሮ በብሄራዊ ማህበሩ ተቀጣሪ አቀነባባሪነት ቡድናዊ የቦርድ አባላት ምርጫ ተከናውኗል።

4.  ምርጫውንተከትሎክክብ መደረግ ሲገባው እስካሁን በዕንጥልጥል ላይ ነው።

5.  የነባሩንቦርድፕሬዚዳንትናምክትልፕሬዚዳንትጨምሮየስራጊዜያቸውንበፈጸሙየቦርድአባላትምትክከተመረጡት  አዲስ የቦርድ አባላት መካከል ሁለቱ በተለይም የማህበሩ የቀድሞ አባላት ከመሆናቸውም ሆነ ካላቸው ተቆርቋሪነት፤ ችሎታና ልምድ አንፃር ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደርጋሉ ተብለው የሚታመንባቸው ዶሰለሞንዓሊናአቶጌታቸውበለጠየተካሄደው ምርጫና እየተካሄደ ያለውን አሰራር በመቃወም ከቦርድ አባላትነት ራሳቸውን ለማግለል ተገደዋል።

6. ራሱንበቡድንአደራጅቶየጠቅላላጉባኤውንድምጽበመንጠቅበተፈጸመውየሕግጥሰትላይየማህበራትኤጀንሲየማስተካከያርምጃእንዲወስድበ25/07/2009 የተፃፈበአባላትየድጋፍፊርማየተደገፈ(Petition) አቤቱታ እንዲሁም

7.  ተካሄደ የተባለው ምርጫ ሕግን፤ ደንብንና ሥርዓትን ያልተከተለ ከዲሞክራሲዊ አሰራር ያፈነገጠ የቡድናዊ አሰራር ውጤት ከመሆን ባለፈ በኤጀንሲው ተቀባይነት አገኝቶ ሊጸድቅ አይገባውም ሲሊ ነባሩ ቦርድ ያስተላለፈውን የውሳኔ ቃለ ጉባኤ ለኤጀንሲው የሰጠ ቢሆንም “ኤጀንሲው ጆሮ ዳባ ልበስ” ብሎ “እስኪጣራድረስአዲሱቦርድስራውንይቀጥልሲልፍትሀዊምላሽከሰጠእነሆወራትአልፈዋል።

ከኤጀንሲው የሚጠበቀው ውሳኔ በመዘግየቱ በማሀበሩ ህልውና ላይ አደጋ ተደቅኗል የወወክማን 70ኛ ዓመት ክብረ በዓል ከማክበር ጋር ሀገራችን የአፍሪካ ኅብረት መቀመጫ ከመሆኗ አንፃር በኬንያ ናይሮቢ የሚገኘውን የአፍሪካ ወወክማ ጽቤትንወደአዲስአበባለማዛወር የነበረው ጥረት በአጭሩ ተቀጭቷል።

በዚህ የሃገር ገጽታን በሚገነባ አኩሪ ተግባር ላይ ጠንክሮ መስራት ሲገባ ሩጫው የበረታው በምረጡኝ ዘመቻ ላይ ነው።

የ70ኛ ዓመት በዓሉም ሳይጀመርና ሳይከበር በዓሉ ተጠናቀቀ ተብሏል። የተቋቋሙ ኮሚቴዎችም ፈርሰዋል።

በአጠቃላይ በማህበሩ መተዳደሪያ ደንብም ሆነ በበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት ኤጀንሲ ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር፣ 621/2009 አንቀጽ 5 (2) መሠረት ማህበራት የሚመሩት በአባላት ተሳትፎ በሚመረጡ ሰዎች እንደሆነ የተደነገገ ሲሆን፤ የጠቅላላ ጉባኤው ምልአተ ጉባኤ ባልተሟላበት የተደረገው ምርጫ ሕጋዊ ስላልሆነ ሊሰረዝ ይገባዋል። እስካሁን ድረስም ምልአተ ጉባኤ በተሟላበት ሁኔታ ምርጫው ስለመደረጉ በማስረጃም አልተረጋገጠም።

ስለሆነም በጉዳዩ ላይ ውሣኔ እስኪሰጥ ድረስ ነባሩ ቦርድ ሥራውን እንዲቀጥል መደረግ ሲገባው በሕግ ጥበት የተመረጡ የቦርድ አባላት ሥራቸውን እንዲቀጥሉ ከኤጀንሲው የተሰጠው ምላሽ ፍትሐዊ አይደለም በሕግም አይደገፍም።

በ1943 ዓ.ም የወጣው የወወክማ ማቋቋሚያ አዋጅ፣ በአዋጅ ያልተሻረ ስለሆነ ሊከበር ይገባል።

ስለዚህ በአዋጅ አንቀጽ 61 መሠረት ኤጀንሲው የማህበሩን ጠቅላላ ጉባኤ የመጥራት ሥልጣን ስላለው በሥራ ላይ ያለውን ቦርድ አግዶ በሕጉ መሠረት የቦርድ አባላትን የማስመረጥ ኃላፊነቱን መወጣት ይጠበቅበታል።

ይህ እንዲሆን ካልተደረገ በአዋጁ አንቀጽ 5(2) ግልጽነትና ተጠያቂነት የሰፈነበትን የመልካም አስተዳደር አሠራርን ኤጀንሲው በተግባር ላይ ለማዋል የተቸገረበት ሁኔታ ጥርጣሬ ውስጥ የሚከተው ይሆናል።

 

 

ወወክማን እንታደገው

ከይሄይስ መኩሪያ

የአዲስ ከተማ ወወክማ (የኢትዮጵያ ወጣት ወንዶች ክርስቲያናዊ ማህበር) አባል ነበርኩ ለከፍተኛ ትምህርት ትግራይ እገኛለሁ።

ባለፈው ጥር ወር ላይ የኢትዮጵያ ወወክማ 70ኛ ዓመት ክብረ በዓል እንደሚከበር ከማህበራዊ ሚዲያ መረጃውን እንዳገኘሁ የመቀሌ ወወክማን ወክዬ ተሰጥኦ ባለኝ የስፖርት ዓይነት ለመወዳደር ተዘጋጅቼ ነበር። ክብረ በዓሉ በልዩ ልዩ ውድድሮች እንደሚታጀብ ስለተገለፀ እንደ እኔው በውድድሮች ለመሳተፍ በርካቶች ጓጉተው ነበር።

ትምህርት ቤት ሲዘጋ እዚህ አዲስ አበባ እንደመጣሁ በወወክማ የቦርድ አባላት ምርጫ ላይ ውዝግብ እንደተነሳ ነሐሴ 10 ቀን 2009 ዓ.ም በጋዜጣችሁ ታትሞ ከወጣው ዘገባ ለመረዳት ችያለሁ።

በሀገር ውስጥና በውጭ ያሉ የቀድሞና የአሁን የወወክማ አባላት ከፍተኛ ተነሳሽነት በየማህበራዊ ሚዲያው እየተስተጋባ የወወክማን ትንሣኤ በበዓሉ እንደሚረጋገጥ ተጠብቆ ነበር። ግና ምን ያደርጋል በዓሉ መከበር ሳይጀምር ተጠናቋል ተባለ።

በርካታ ሰዎች በበዓል አዘጋጅ ኮሚቴ አባልነት የተለመደውን የወወክማን የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ለመስጠት ተዘጋጅተው ሳለ ቦርዱ ኮሚቴዎቹን በትኖ በተጓደሉ የቦርድ አባላት ምትክ ምርጫ ማድረጉን ሰማን በየትም ቦታ ያለ የወወክማ አባል በጠቅላላ ጉባኤው ለመገኘት ለመምረጥም ሆነ ለመመረጥ መብት አለው። ይህ በደንቡ የተረጋገጠ መብት ያለው የማህበሩ አባል በጠቅላላ ጉባኤው እንዲሳተፍ ጥሪ ያልተላለፈበት ሁኔታ የሕግ ጥሰት ነው።

ምልአተ ጉባኤ ሳይሟላ የተደረገው ምርጫም ሕጋዊ ስላልሆነ መሠረዝ ይኖርበታል።

የታቀደውን በዓል ለማስከበር ያልቻለ ቦርድም በሥራ ላይ ሊቀጥል አይችልም። የወወክማ የቦርድ አባላት ለ2 ጊዜያት የምርጫ ዘመን ብቻ እንደሚያገለግሉ በሕገ ማህበሩ ተደንግጓል።

አሁን ተደረገ የተባው ምርጫ የሥራ ዘመናቸውን በጨረሱ የቦርድ አባላት ምትክ እንደሆነ ተገልጿል።

በመሠረቱ የሥራ ዘመናቸውን ያልጨረሱትስ በደካማነታቸው የተነሳ የበዓሉ አከባበር ተደናቅፏል።

ስለሆነም የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት ኤጀንሲ ዝምታውን ሰብሮ በሕግ በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ራሱ የጠቅላላ ጉባኤ ጠርቶ የአዲስ የቦርድ አባላት ጠቅላላ ምርጫ እንዲከናወን ማድረግ ይጠበቅበታል።

ኤጀንሲው በርካታ የሰው ኃይልን ይዞ በተንጣለለ ጽ/ቤቱ ይህን ቀላል ጉዳይ በወቅቱ ለመፍታት ያልቻለበት ሁኔታ አሉታዊ ጥርጣሬ ውስጥ ይከታል።

ኤጀንሲው ችግሩን ለመፍታት ካልቻለ በአዋጅ ቁጥር 621/2009 ዓ.ም ኤጀንሲውን የሚቆጣጠረው ቦርድ መፍትሄ እንዲሰጥ ለማሳሰብ እንወዳለን። 

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
119 ጊዜ ተነበዋል

ተጨማሪ ጽህፎች ከ news admin

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 979 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us