ሚድሮክ ወርቅ ማዕድን የሳካሮ ወርቅ ማዕድን የልማት ሥራን ይመለከታል

Wednesday, 08 February 2017 15:09

ጥር 21 ቀን 2009 ዓ.ም በወጣው የአማርኛ ሪፖርተር ጋዜጣ ቅጽ 22 ቁጥር 1748 ላይ የቀረበውን ዘገባ በመረጃ ያልተደገፈ፣ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ያላካተተ እና ያላገናዘበ ሆኖ አግኝተነዋል። በመሆኑም ይህን ማብራሪያ እንደሚከተለው አቅርበናል።

በተጠቀሰው ዘገባ ላይ የተፈጥሮ ሃብት ልማትና የአካባቢ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ የማዕድን፣ ነዳጅና የተፈጥሮ ጋዝ ሚኒስቴርን ጥር 17 ቀን 2009 ዓ.ም የስድስት ወራት የሥራ አፈፃፀም ሪፖርት በተሰማበት ወቅት የፓርላማ የቋሚ ኮሚቴው ምክትል ሰብሳቢን በመጥቀስ ሚድሮክ ወርቅን የመንግሥት ጥቅም ከሚያስቀሩ ኩባንያዎች ጐራ ሊመድብ ሞክሯል።

ምክንያት ያደረገው “ባለፉት ሁለት ዓመታት የሳካሮ ማዕድን ሙከራ ላይ ነው እየተባለ ነገር ግን ምርት እየተከናወነ ነበር” በመሆኑም የመንግሥት ጥቅምን አስቀርቷል በሚል ነው።

አንድ የማዕድን ሥራ በልማት (በሙከራ) የሚቆይበት ጊዜ እንደ ማዕድኑ አሠራር፣ ባሕሪና ጂኦሎጂ የሚለይ ቢሆንም፣ የሳካሮ ማዕድን በልማት ወቅት ከተመረተው የወርቅ ምርት የመንግሥትን ጥቅም በምንም መልኩ አላስተጓጐለም።

ከሳካሮ የተመረተ ወርቅ የልማት ጊዜ (ሙከራ) ምርት ይባል እንጂ በሙከራ ጊዜም ሆነ በምርት ጊዜ የሚመረት ወርቅ እንደ ምርት ተቆጥሮ የሚሸጥ፣ ገቢውም በሕጉ መሠረት የሚመዘገብና ለመንግሥት የሚከፈለውም ገንዘብ የሚከፈል ነው። ስለሆነም በሙከራ ጊዜ የተመረተውና በምርት ጊዜ የሚመረተው ሁለቱም እንደ ምርት ተቆጥረው የሚስተናገዱ መሆናቸውን ካለመገንዘብ በስህተት የኩባንያውን ስም ለማጉደፍ መሞከሩ ተገቢ አይደለም። በተለይም ለሚድሮክ ወርቅ ኃላፊዎች አንድም መጠይቅ ሳይቀርብ እና ማብራሪያ ሳይጠየቅ የተመሰከረለት ጥራት ያለው ሥራ የሚሠራ ኩባንያ አለአግባብ ስሙን ማጥፋት ተገቢ አይመስለንም። ወደ ውጭ ሀገር መላኩ ላይ የጉምሩክና የብሔራዊ ባንክ ተወካዮች ባሉበት የሚከናወን ሥራ መሆኑም መታወቅ አለበት።

የሳካሮም ሆነ የለገደምቢ ማዕድኖች ያመረቱት ምርት ዕቅድ የየዓመቱ እና የአምስት ዓመቱ ሪፖርት ለማዕድን ሚኒስቴር ቀርቧል። በዚህ መሠረትም ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ክትትል ያደርጋል።

ስለሆነም በዚህ ረገድ የሳካሮ ማዕድን በልማት በቆየበት ጊዜ የመንግሥትን ጥቅም ያስቀረንበት አንድም ሁኔታ አለመኖሩን ሁሉም እንዲያውቀው ያስፈልጋል። በተጨማሪም ዘገባ ያቀረበው ጋዜጣ በተመሳሳይ ጉዳይ ከሁሉም አካላት መረጃ ሊጠይቅ እንደሚገባ ልናስታውስ እንወዳለን። “ጠይቀን ፈቃደኛ አልሆኑም” የሚለው የተለመደ እውነትነት የጎደለው አገላለጽም ያስተዛዝባልና መታረም ይኖርበታል።

የሚድሮክ ወርቅ ማዕድን ኃላ.የተ.የግ.ማኅበር¾  

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
544 ጊዜ ተነበዋል

ተጨማሪ ጽህፎች ከ news admin

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 1027 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us