ከኢትዮጵያ ፍትህና ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች ግንባር /ኢፍዴኃግ/ የተሰጠ መግለጫ

Wednesday, 21 January 2015 15:48

ሰሞኑን በሱዳን ከተማ ካርቱም የሶስትዮሽ የአባይ የህዳሴ ግድብ አስመልክተው ውይይት ማድረጋቸው ሰምተናል። ይህ የሦስትዮሽ መንግሥታት የህዳሴ ግድብ አስመልክተው መወያየታቸው እና በመጨረሻም በስምምነት መጨረሳቸው በጣም ልንደግፈው የሚገባው እርምጃ በመሆኑ ይበል ሊባል ይገባዋል ብለን እናምናለን።

ኢትዮጵያ ሀገራችን ለዘመናት ህዝብን በአግባቡ ከመመገብና ፍላጎቱን ለማሟላት ተስኗት ሁሌ የዕርዳታና የልመና ታሪክ ተሸክማ የቆየቻቸው ዘመናት ሁሉ ስናስባቸው ሳናጣ ያጣ መቸገር የማይገባን ስንቸገር ዕውቀት ሳይጠፋ እንደማናውቅ ሀገራችን ለቀኝ ግዛትና ለወራሪዎች ሳንበረከክ /ሳንበገር/ ነፃነታችን ጠብቀን ክብራችን ለልጅ ልጅ ስናሸጋግረው የኖርን ነን። የነፃነት ሐዋሪያዎች አባቶቻችን የነገሩንና ያስረከቡን የኩሩ ህዝቦች ልጆች ስንሆን ለዕድገትና ለብልፅግና ግን ገና አሁንም ገና በጣም ብዙ ጉዞና ትግል የሚጠበቅብን ሕዝብ ብንሆንም የዕድገትና የብልፅግና ጊዜያችን ዛሬ ተያይዘነው በተስፋ ሰጪ ጎዳና ላይ እንደምንገኝ ግልጽ ነው።

ከፋሽስታዊ ደርግ ውድቀት በኋላ ኢትዮጵያ ሀገራችን በብዙ ዓይነት የመልካም ተስፋ ሰጪ የሰላም፣ የልማት፣ የዴሞክራሲ ጅማሮ የመፃፍ፣ የማንበብ እና ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ ነፃነት ሁሉ እስከነ ችግራቸው መልካም ጅማሮ ናቸው። እነዚህ ተስፋ ሰጪ ጅማሮዎች ደግሞ ከስሜታዊ ከችኮላ ታግሰን የጎደሉት በመሙላትና በመቻቻል መርህ እየተገዛን ሁልጊዜ የሰላሙ፣ የልማቱ ጅማሮ ሁሉ ዛሬም አንድ እርከን በመጨመር አሁንም በመቻቻል መጥፎውን ነጥብ እያስያዝን ጭልጥ ወደ አለው ስህተት በመሄድ የተጀመሩት ሰላማዊ ልማታዊ ጅምር ከማደናቀፍ ተጠንቅቀን ልንጓዝ ይገዛል። ነገር ግን ስህተቶችን በተጨማሪ ደግሞ የዕድገትና የስልጣኔ ጎዳናዎች እያጠናከርን እሾሆችንና እንቅፋቶችን እየለቀምን የሸክማችን ጫናም በግልፅ በመጠቆምና በማጋለጥ እንዲቃለል በመታገል ነገ ኢትዮጵያ ሀገራችንና ሕዝባችን እንደ ጥንቱ ተከብራ ነገር ግን እየተራብን ሳይሆን እየተከበርን እየጠገብንም በተሟላ የሀገራችን ብልፅግና ያለ ልዩነት በእኩልነት የሀገራችን ጥቅም ለሀገራችን ሁኖ የኢትዮጵያ ሕዝብ የተሟላ ጤና፣ ጥጋብ፣ ክብር፣ ሰላም ሁሉም ነገር ተሟልቶ በሀገራችን ኮርተን ለመኖር ልማታዊ ጅማሮዎን ብንችል ረድተን ካልቻልን ፖለቲካዊ ድጋፉን በግልፅ ሰጥተን ሀገራችን ኢትዮጵያ የተያያዘችውን የልማት ትግል ለሀገራችንና ለሕዝባችን ለእውነተኛ ግባችንም እውነተኛ ድጋፍ ልንሰጥ ይገባል።

ኢትዮጵያ ሀገራችን ከወሰደቻቸው የልማቶች ሁሉ የበላይና ለኢትዮጵያነታችን ላይ ቁመን ልዩነት በሌለው አብረን የዘመርንለትን ድጋፋችን የቼርነሌት የህዳሴው ግድባችን አንዱ ነው።

የኢትዮጵያ መንግስት መጋቢት 24 ቀን 2003 ዓ.ም በአባይ ወንዝ የመሰረተ ድንጋይ ካስቀመጠበት ቀንና ዘመን ጀምሮ የኢትዮጵያ ሕዝብ ምንም ይሁን ምን ልዩነት ቢኖረንም በህዳሴው ግድብ የተወሰደው አቋም ግን የኢትዮጵያ ሕዝብ ማህንዲሱ ገንዘቡም ሥራውን የራሱ በማድረግ ያለ ምንም ዓይነት እርዳታና ልመና ሳይፈልግ አባይ ይገደባል የሚል አቋም፣ ከተገለፀና ከታወጀበት ዕለትና ቀን ጀምሮ ብዙ ድጋፍ የሰጠም ብዙ ጠላትም የተነሳበትም ነበር። አብዛኛው የተፋሰሱ ሀገራት ድጋፋቸው በፊርማቸው እንደ አረጋገጡት ሁሉ ሁለት የተፋሰሱ አገራት ሳይፈርሙ በተለይ የግብፅ መንግስት እንኳንስ ሊፈርምና ድጋፍ በመስጠት ኢትዮጵያ መብትዋና ድርሻዋን ገደብ ለመጠቀም የሚችለው ፍቃዱ ከኔ ከግብፅ መንግስት ስታገኝ ነው እስከማለት ደርሳለች። ስለሆነም እኔ ሳልፈቅድ በአባይ ወንዝ ምንም ዓይነት የቁፋሮ ስራ እንዳይሞከር ዓይነት ማስፈራሪያ /ማስጠንቀቂያ/ በመስጠት እንዲሁም የተፋሰሱን ሀገራት ለምን ፈረማችሁ ችግሩ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ሰበቡ ለእናንተም ይተርፋል እያለች ከፍተኛ ጫና በመፍጠሯ የኢትዮጵያ ዜጎች እራሳቸው የግብፅ ደጋፊዎም እስከምን ሆን ሁሉ ታሪክ አስተምሮናል።

የኢትዮጵያ መንግስትና ሕዝብ ግን በዓባይ በኩል የሚመጣው ሁሉ ያለምንም ማቅማማት እንመክተዋለን። የልማት ሥራችንም ለቀናት ቀርቶ ለደቂቃዎች ማቆም እንደማንችል ብሎ በያዘው አቋም ምክንያት ግብፅ ከማስፈራራትና አጉል ትዕቢት አቋሟ እደራደራለሁ ለማለት መድረስዋ ለኢትዮጵያ መንግስትና ሕዝብ የድል ሁሉ ድል ትልቁ የልማታዊ ድል መሆኑን ኢፍዴኃግ በኩራት ይገልፀዋል። ኢትዮጵያ ሀገራችን እና በታሪክ የአንድ ህዝብ መብትና ጥቅም ለመቀልበስ ተነስተን አናውቅም።

ነፃነታችንንም አስነክተን አናውቅም፤ ይህን ታሪካዊ ጀግነታችን ዛሬ በልዩ ትርጉም የምንገልፀው አንደኛ ድሮ ድሮ ጀግንታችን ለነፃነትም ብቻ የነበረ ሲሆን በዛሬው ጀግንነታችን ግን በሁለት ጀግንነት ነው የምንገልጸው።

  1. ጀግንነት ለነፃነታችን ሲሆን፣
  2. ጀግንት ለነፃነታችን ለኢኮኖሚ ዕድገትም ጭምር መሆኑ ነው።

ስለሆነም የኢትዮጵያ ፍትህና ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች ግንባር /ኢፍዴኃግ/ የኢትዮጵያ መንግስት በወሰደው ፍትሐዊ የመብት ማስከበር እና የህዝብን ጥቅም በልማት ችግሩን የመፍታት ትግል ጠላት አምበርክከዋል።

በመሆኑም አሁንም ቢሆን የኢትዮጵያ መንግስት ሊገነዘበው የሚገባው ከግብፅና ከሱዳን መንግስታት ያደረገው ምክክርና የደረሰበት ግብ የሚያኮራን ቢሆንም ከነበረው አቋም ያለምንም መሸራረፍ በነበረው አቋሙና ዓላማው በመፅናት ኢትዮጵያዊነት ታሪካዊ ህዝባዊ አቋሙ መቀጠል ይገባዋል ብለን እደ ኢፍዴኃግ እና እንደ የህዳሴ ብሔራዊ ም/ቤት አባልነታችን እናሳስባለን።

                  የህዳሴ ግድባችን ህይወት

                  ለመጠበቅና ወደ ውጤት

                  ለማድረስ በርትተን እንረባረባለን

                  ኢትዮጵያ ለዘለአለም ትኑር።

 

                  ጥር 9 ቀን 2007 ዓ.ም

ከኢትዮጵያ ፍትህና ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች ግንባር /ኢፍዴኃግ/ ጽ/ቤት

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
815 ጊዜ ተነበዋል

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us