ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

Wednesday, 14 January 2015 12:00

አዲስአበባ


የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ታኅሣሥ 28 ቀን 2007 ዓ.ም በቁጥር አ/573/ፖአ/ጠ407 የፃፈውን ደብዳቤ በጥር 1 ቀን 2007 ዓ.ም ደርሶን ተመልክተነዋል። ምርጫ ቦርድ በዚህ ደብዳቤ በርካታ ውንጀላዎችን በሰማያዊ ፓርቲ ላይ ያካሄደ ቢሆንም፤ በፓርቲያችን በኩል ዋና ዋና ናቸው ባልናቸው ላይ ብቻ እንደሚከተለው ምላሽ ሰጥተንባቸዋል።

1ኛ. “ሰማያዊ ፓርቲ ሕጋዊ እውቅና ሳያገኝ እንዳለው አድርጎ የተለያዩ መግለጫዎችን ሰጥቷል” በሚል የቀረበውን ውንጀላ ፓርቲያችን አይቀበለውም። ፓርቲያችን ለቦርዱ ያቀረበውን የዕውቅና ጥያቄ ምላሽ በተሻሻለው የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ አዋጅ ቁጥር 573/2000 አንቀፅ 9 ንዑስ አንቀፅ 5 መሰረት በሦስት ወር ጊዜ ውስጥ መልስ ካልሰጠ በዚሁ አዋጅ አንቀፅ 9 ንዑስ አንቀፅ 7 መሰረት የምዝገባ ማመልከቻ ያቀረበው የፖለቲካ ፓርቲ በቦርዱ እንደተመዘገበ ስለሚቆጠር፣ ይህንኑ ሕጋዊ መብቱን በመጠቀም ፓርቲያችን ሕጋዊነቱን አውጇል። ይህም ድርጊታችን ሕጋዊ ስለነበር በቦርዱ በኩል የሕጋዊ ዕውቅና የምስክር ወረቀቱን ከመስጠት ውጭ ምንም ዓይነት ክስም ሆነ ውንጀላ በወቅቱ አላቀረበም።

2ኛ. “ሰማያዊ ፓርቲ በተለያዩ አፍራሽ ተግባራት ውስጥ እየተሳተፈ ይገኛል” በማለት የቀረበው ውንጀላ በዚሁ ደብዳቤ እንደ አብነት ከተጠቀሱት ውንጀላዎች መረዳት እንደሚቻለው በተለያዩ ጊዜያት በቦርዱ የተጠሩ ስብሰባዎችን እየተወ ይወጣል የሚል ሆኖ አግኝተነዋል። ፓርቲያችን እስካሁን በተካሄዱት ስብሰባዎች ላይ አጀንዳዎች እንዲያዙለት የሚያቀርባቸው ጥያቄዎች በተደጋጋሚ በቦርዱ በኩል ውድቅ እየተደረጉ ቦርዱ “የእኔን አጀንዳ ብቻ ስሙኝ” ባለባቸው ስብሰባዎች ላይ ሙሉውን ጊዜ ለመሳተፍ ፍላጐትም ሆነ ግዴታ አልነበረበትም። ወደፊትም ቢሆን ቦርዱ በተመሳሳይ አቀራረብና የስብሰባ ይዘት የሚቀጥል ከሆነ ስብሰባዎችን እየተውን የምንወጣ መሆናችንና ይህም ባላመንበት አጀንዳ ላይ ያለመሳተፍ ሕጋዊ መብታችን መሆኑን እያረጋገጥን በዚህ በኩል የቀረበን ውንጀላ ተቀባይነት የሌለው መሆኑን እንገልፃለን።

3ኛ. “ሰማያዊ ፓርቲ ከተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ከቦርዱ እውቅና ሳያገኝ ትብብር የሚባል አደረጃጀት መስርቶ ሕገወጥ እንቅስቃሴ አድርጓል” የሚል ውንጀላ ቦርዱ አቅርቧል። በተሻሻለው የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ አዋጅ ቁጥር 573/2000 አንቀፅ 32፣ 34 እና 35 መሰረት የቦርዱን እውቅና የሚፈልጉት አደረጃጀቶች ውህደት፣ ግምባርና መቀናጀት መሆናቸውን ደንግጓል። ከእነዚህ ውጭ የፖለቲካ ፓርቲዎች በሚያግባቧቸው የጋራ ጉዳዮች ላይ ተነጋግረውና ተባብረው መሥራታቸው በየትኛውም ሕግ የተከለከለ አይደለም። በመሆኑም ፓርቲዎች በእኩልነት የሰሩትን ሥራ ያለምንም ማስረጃ “ሰማያዊ ፓርቲ እያስተባበረ ነው” በማለት የቀረበው ውንጀላ መሰረተ ቢስ ከመሆኑም በላይ ቦርዱ የፓርቲዎችን በነፃነት የመንቀሳቀስ ሕጋዊ መብት እየተጋፋ መሆኑን አውቆ ከዚህ ዓይነቱ ውንጀላ እንዲቆጠብ እንጠይቃለን።

በመጨረሻም፤ ቦርዱ በላከው ደብዳቤ ላይ ያቀረባቸውን ውንጀላዎች መሰረት በማድረግ ፓርቲያችን ይቅርታ እንዲጠይቅ ያቀረበው ውሳኔ ከላይ በዘረዘርናቸው ተጨባጭ እውነታዎች መሰረት ተቀባይነት የለውም። ከዚህም በተጨማሪ ይህ ዓይነቱ የይቅርታ ጠያቂና የይቅርታ አድራጊ ግንኙነት ለምርጫ ቦርድ በሕግ ከተሰጡት ስልጣንና ተግባራት ውጭ በመሆኑ የቦርዱ እና የፖለቲካ ፓርቲዎች ሕጋዊ ግንኙነትን ያልተከተለና ተቀባይነት የሌለው መሆኑን እንገልፃለን።

ከአክብሮት ጋር

ይልቃል ጌትነት መሸሻ

                                                        የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር

ይምረጡ
(1 ሰው መርጠዋል)
1180 ጊዜ ተነበዋል

ተጨማሪ ጽህፎች ከ news admin

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 1060 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us