በእርሻ ኢንቨስትመንት ለተሰማሩ የሀገር ውስጥ ባለሃብቶች ብድር ማራዘሚያ ተፈቀደላቸው

Friday, 12 January 2018 16:57

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለሀገር ውስጥ የእርሻ ኢንቨስትመንት ባለሃቶች ከዚህ ቀደም ላቀረቡት የብድር ማራዘሚያ ጥያቄ ፈቃድ መስጠቱ ታውቋል፡፡

የልማት ባንክ አነስተኛ መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ፋይናንሲንግ ም/ፕ አቶ ተሾመ አለማየሁ ታህሳስ 3 ቀን 2010 ዓ.ም. በውስጥ ማስታዋሸ ለባንኩ ሰራተኞች በሰጡት ትዕዛዝ፣“ለሚቀጥለው ዓመት የእርሻ ወቅት ከመድረሱ በፊት ደንበኞን እንደሥራ አፈፃፀማቸው በመገምገም የብድር ማራዘሚያና የሥራ ማስኬጃ ብድር የሚያስፈልጋቸውን በመለየት ከወዲሁ ዝግጅት እንድታደርጉ አሳስባለሁ” ብለዋል፡፡

እንዲሁም፣ ሕዳር 24 ቀን 2010 ዓ.ም የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የበላይ አመራር ባደረገው ጥሪ መልካም አፈፃፀም ካላቸው በባንኩ የብድር ድጋፍ የተቋቋመ በዝናብ ከሚለሙ እርሻ ፕሮጀክት ባለሀብቶች ጋር የጋራ የምክክር ስብሰባ አድርጓል፡፡ በዚህም ስብሰባ ላይ ባንኩና ደንበኞቹ የጋራ ጉዳዮቻቸው ላይ ሰፋ ያለ ውይይት ካካሄዱ በኋላ ደንበኞ የሚከተሉትን ዋና ዋና ነጥቦች ማለትም፤ በየጊዜው ክትትል አታደርጉም ማለትም በአመት ሶስት ጊዜ (በዘር፣ በአረምና በምርት ስብሰባ) እንዲሁም የሥራዎቻችንን አፈፃፀም አታዩልንም፤ ችግሮቻችንን በቅርበት አይታችሁ  የምትደግፉን ከሆነ ክፍያ ለመፈፀም ዝግጁ ነን፤ ከባንኩ ጋር ያለን ግንኙነት ደካማ ነው ተቀራርቦ መሥራት የለም፤ ደንበኞችንና ፕሮጀክቱን አታውቋቸውም፣ የሚሰራውንና የማይሰራውን አትለዩም፤ በግብርና ወቅት የጠበቀ የብድር አለቃቀቅ አትከተሉም፤ ኢንሹራንስን በተመለከተ ያለው አሰራር ግልፅ አይደለም እና የመሳሰሉት አስተያየቶች መስጠታቸው ይታወሳል፡፡

በዚህ መነሻ ም/ፕሬዝደንቱ በሰጡት ትዕዛዝ እንዳሉት፣ “በየወቅቱ የተሟላ የክትትል ሥራ መሥራት፣ ደንበኞችን ያጋጠማቸውን ችግሮች ገምግሞ የተለያዩ መፍትሄዎች ለምሳሌ ብድር ማራዘሚያ ተጨማሪ ብድር መስጠት ወዘተ የመሳሰሉት የመፍትሄ እርምጃዎች መውሰድ ከሁሉም በላይ ብድሮችን መሰብሰብ የዲስትሪክቶች ዋናው ሥራ ስለሆነ መርሃ-ግብር በማዘጋጀት ከላይ የተዘረዘሩትን ሥራዎች በመሥራት አፈፃፀማቸውን በየጊዜው ማለትም በየወሩ ሪፖርት እንድታደርጉ እየገለፅኩ፣ ለሚቀጥለው ዓመት የእርሻ ወቅት ከመድረሱ በፊት ደንበኞን እንደሥራ አፈፃፀማቸው በመገምገም የብድር ማራዘሚያ ና የሥራ ማስኬጃ ብድር የሚያስፈልጋቸውን በመለየት ከወዲሁ ዝግጅት እንድታደርጉ አሳስባለሁ” ብለዋል፡፡

በዚህ የውስጥ ደብዳቤ መነሻ እና ከፍተኛ የባንኩ ኃላፊዎች በስፋት ከተወያዩ በኋላ በባለሃብቶቹ ሲቀርብ ለነበረው የብድር ማራዘሚያ ጥያቄ ፈቃድ መስጠታቸውን የባንኩ ታማኝ ምንጮቻችን ገልጸዋል፡፡

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
158 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 1020 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us