የሰሞኑ የኤርትራና የግብፅ ወታደራዊ ግንኙነት ውዝግብን ፈጥሯል

Friday, 12 January 2018 16:44

ግብፅ በከፍተኛ ደረጃ የታጠቀ ጦር ኃይሏን ወደ ኤርትራ ምድር መላኳን ተከትሎ ሱዳን የኤርትራ አዋሳኝ ድንበሯን ዘጋች የሚሉ ተከታታይ ዘገባዎች ከሰሞኑ ሲወጡ ከርመዋል፡፡

ሱዳን በበኩሏ ድንበሯን የዘጋችው ከኤርትራ ጋር በሚያዋስናት ከሰላ ግዛት ያወጀችውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተግባራዊ ለማድረግ መሆኑን እየገለፀች ነው፡፡  የሱዳን መንግስት በኤርትራ አዋሳኝ ድንበር አካባቢ ያሉትን ታጣቂ ኃይሎች ለመቆጣጠርና ትጥቅ ለማስፈታት እንደዚሁም በአካባቢው በተለይም ከኤርትራ ወደ ሱዳን በህገወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች የሚፈልሱትን ስደተኞች ለመቆጣጠር ድንበሩን መዝጋቱን አስታውቋል፡፡

የሱዳን ዜና አገልግሎት ሱናን ጠቅሶ ዘገባውን ያሰራጨው የቻይና ዜና አገልግሎት ዥኑዋ በሺዎች የሚቆጠሩ የሱዳን ጦር ኃይል አባላት ኤርትራን በምታዋስነው የከሰላ ግዛትና በሱዳን ኤርትራ ደንበር የሰፈሩ መሆኑን ገልጿል፡፡

ይሁንና በሌላ አቅጣጫ የሚወጡ ዜናዎች እንደሚያመለከቱት ከሆነ ደግሞ ሱዳን በኤርትራ በኩል ያላትን ድንበር ለመዝጋት የተገደደችው ግብፅ በሚገባ የታጠቀ ጦር ኃይሏን ወደ ኤርትራ ምድር ማስገባቷን ተከትሎ ነው፡፡ እንደ ሚድል ኢስት ሞኒተር ዘገባ ከሆነ የግብፅ ጦር ወደ ኤርትራ ምድር ሳዋ ያመራው ከተባበሩት አረብ ኤሜሬቶች እና ከሱዳን መንግስት ተቃዋሚ ሀይሎች ጋር በመተባበር ነው፡፡

እንደዘገባው ከሆነ ግብፅ ጦሯን ወደ ኤርትራ ምድር ያስገባቸው ቱርክ በቅርቡ ሱአኪን በተባለች የጥንት የሱዳን ወደብና ደሴት ላይ ወታደራዊ ቤዝ ለመገንባት ማቀዷን ተከትሎ ነው፡፡ ግብፅ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በምስራቅ አፍሪካ የቀይ ባህርና ህንድ ውቅያኖስን ተከትሎ ያላትን ወታደራዊ አድማስ ለማስፋት በመስራት ላይ ስትሆን እንደ ሚድል ኢስት ሞኒተር ዘገባ ከሆነ 20 ሺህ እስከ 30 ሺህ ጦር ማስፈር የሚያስችላትን ወታደራዊ ቤዝ ለማግኘት ለሶማሊያና ለጂቡቲ መንግስታት ጥያቄ አቅርባለች፡፡

 ግብፅ ተመሳሳይ ወታደራዊ ቤዝ በኤርትራ ቀይ ባህር ዳርቻ ያቋቋመች መሆኑን አንዳንድ የሚወጡ መረጃዎች ቢያመለክቱም ግብፅም ሆነች ኤርትራ እነዚህን ዘገባዎች በጥብቅ ሲያስተባብሉ ቆይተዋል፡፡ ግብፅ ይህንን መረጃ እያስተባበለች ባለችበት ሁኔታ  ጦሯ ከሰሞኑ በኤርትራ ሳዋ ምድር ገብቷል የመባሉ ጉዳይ እጅግ አነጋጋሪ ሆኗል፡፡

ግብፅ ከተወሰኑ ዓመታት ወዲህ ከሱዳን መንግስት ጋር አለመግባባት ውስጥ የገባች ሲሆን እነዚህም አለመግባባቶች በሁለት መሰረታዊ ጉዳዮች የተመሰረቱ ናቸው፡፡ አንደኛው ቀደም ሲል በሁለቱ ሀገራት መካከል በነበረው የድንበር ግዛት ይገባኛል እየተካረረ መምጣቱ ሲሆን፤ ሁለተኛው ጉዳይ ሱዳን የህዳሴውን ግድብ በተመለከተ ለኢትዮጵያ ድጋፏን መስጠቷ ነው፡፡ ሁለቱ ሀገራት የተካረረ ውዝግብ ውስጥ መግባታቸውን ተከትሎ የህዳሴውን ግድብ በተመለከተ ሶስቱ ሀገራት ማለትም ኢትዮጵያ፣ ግብፅ እና ሱዳን ከሚያደርጉት የሶስትዮሽ ውይይት ሱዳን እንድትወጣ ግብፅ በይፋ ጥያቄ እስከማቅረብ ደርሳለች፡፡ አካባቢው ይህንን በመሰለ ወታደራዊ ውጥረት በገባበት ሁኔታ ትናንት ማክሰኞ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ ወደ ካይሮ በመብረር ከፕሬዝዳንት አብዱል ፈታህ አልሲሲ ጋር ተገናኝተዋል፡፡ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ በዚሁ ይፋዊ ጉብኝታቸው በግብፅ ሁለት ቀናትን የሚያሳልፉ መሆኑ በዚሁ ዙሪያ የወጡ ዘገባዎች ያመለክታሉ፡፡

የዚሁ ዘገባ ምንጭ የሆነው የግብፁ ሜና የዜና ወኪል በፕሬዝዳንት ኢሳያስ ጉብኝት የሱዳንና የአባይ ተፋሰስ ሀገራት ጉዳይ እንደዚሁም የአፍሪካ ቀንድ የፖለቲካ ጉዳይ በአጀንዳነት የሚነሳ መሆኑን አስታውቋል፡፡ ኤርትራ በናይል ቤዝን ኢንሼቲቭ ላይ ከታዛቢነት ያላላፈ ሚና ያልነበራት ሀገር ከዚያም ባለፈ ከኢትዮ ኤርትራ ጦርነት በኋላ በዚህ ዙሪያ ምንም ሚና ያልነበራት ብትሆንም በምን መልኩ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ እንደሚወያዩ ግልፅ አይደለም፡፡ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ ካይሮ በተከታታይ ሲመላለሱ የቆዩ ሲሆን ይህ የሰሞኑ ጉብኝታቸው ለአምስተኛ ጊዜ መሆኑን ጉብኝቱን ተከትሎ የወጡ ዘገባዎች ያመለክታሉ፡፡ ሱዳን ቀደም ብላ በካይሮ የሚገኙትን አምባሳደሯን ለውይይት የጠራች መሆኗን ዘገባዎች አመልክተዋል፡፡

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
212 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 1022 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us