የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 2 ስኳር ፋብሪካ እንደገና ማምረት ጀመረ

Wednesday, 03 January 2018 16:04

ከሙከራ ምርት በኋላ ወቅቱን ባልጠበቀ ዝናብ ምክንያት ላለፉት ስድስት ወራት ከምርት ውጪ ለመሆን ተገድዶ የነበረው  የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 2 ስኳር ፋብሪካ  ከታህሳስ 22 ቀን 2010 ዓ.ም ጀምሮ ስኳር በማምረት መደበኛ ሥራውን ጀመረ።

ስኳር ከማምረቱ ከሁለት ቀናት በፊት አገዳ በመፍጨት ሥራ የጀመረው ይህ ፋብሪካ ከሰኔ አጋማሽ 2009 ዓ.ም ጀምሮ ስኳር እንዲያመርት ታቅዶ የነበረ ቢሆንም የአየር ንብረት መዛባትን ተከትሎ በአካባቢው ባልተለመደ ሁኔታ በጣለው ከፍተኛ ዝናብ ሳቢያ በወቅቱ ለፋብሪካው ግብዓት የሚውል ሸንኮራ አገዳ ከማሳ በማውጣት ወደ ፋብሪካ መውሰድ አዳጋች ሁኔታ በመፈጠሩ ፋብሪካው ስኳር ማምረት ሳይችል ቀርቷል።

ኮምፕላንት በተባለ የቻይና ኩባንያ የተገነባው ይህ ፋብሪካ በቀን 12 ሺህ ቶን አገዳ የመፍጨት አቅም ያለው ግዙፍ ፕሮጀክት ሲሆን፣ ሙሉ የማምረት አቅሙ ላይ ሲደርስ በዓመት እስከ 2 ነጥብ 5 ሚሊዮን ኩንታል ስኳርና 28 ሚሊዮን ሊትር የሚጠጋ ኤታኖል እንደሚያመርት ይጠበቃል።

ለፋብሪካው ግንባታ ብቻ ከቻይና ልማት ባንክ በተገኘ 6 ነጥብ 67 ቢሊዮን ብር ብድር ሐምሌ 2007 ዓ.ም ሥራው በይፋ የተጀመረው የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 2 ስኳር ፋብሪካ ባጋስ ከተባለ የስኳር ተረፈ ምርት ከሚያመነጨው 60 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ሃይል ውስጥ 20ውን ለራሱ ተጠቅሞ 40 ሜጋ ዋቱን ወደ ብሔራዊ ቋት የመላክ አቅም አለው።

የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 2 ስኳር ፋብሪካ አሁን በምርት ላይ የሚገኙትን ስኳር ፋብሪካዎች (ወንጂ ሸዋ፣ መተሐራ፣ ፊንጫአ፣ ከሰምና ተንዳሆ) ቁጥር ወደ ስድስት አድርሶታል። በተጨማሪ የአርጆ ዲዴሳ ስኳር ፋብሪካ ከጥር ወር መጨረሻ ጀምሮ ወደ ሥራ እንደሚገባ እንደሚጠበቅ ከኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን የተገኘ ዜና ጠቁሟል።¾

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
189 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 1035 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us