የምርጫ ቦርድ አወቃቀር ኢህአዴግን እና ተቃዋሚዎችን አላግባባም

Wednesday, 15 November 2017 12:33

ገዥው ፓርቲ ኢህአዴግ እና 15 የፖለቲካ ፓርቲዎች ድርድር እያካሄዱ ቢሆንም፤ የምርጫ ቦርድ አወቃቀር የማያስማማቸው ነጥብ ሆኗል።

 

በድርድሩ ተሳታፊ የሆኑት መኢአድና ኢዴፓን ጨምሮ 11 ተቃዋሚ ፓርቲዎች ምርጫ ቦርድ አወቃቀሩ ወደ ኮሚሽን ይቀየር ሲሉ አጥብቀው ቢሞግቱም፤ ገዥው ፓርቲ እና አራት ፓርቲዎች ግን ባሉበት እንዲቀጥሉ ሲሉ ተከራክረዋል።


ኢህአዴግ ያቀረበው ሃሳብ የቦርዱ አወቃቀር ባለበት ሆኖ ነገር ግን በተወሰኑ አንቀጾች ላይ ማሻሻያ ይደረግ የሚል ነበር። ማሻሻያ ይደረግባቸው የተባሉ የቦርዱ አወቃቀር አንቀጾች ደግሞ “በምርጫ ቦርድ አባላት ላይ በሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ወንበር ያላቸው ተቃዋሚዎች ብቻ ሳይሆን ወንበር የሌላቸውም እንዲካተቱ በሚል ይተካ” የሚል ነው።


ከኢህአዴግ በተጓዳኝ ያሉ ተቀናቃኝ ፓርቲዎች ግን የቦርዱ አወቃቀር በኮሚሽን ቢተካ ወደ 15 ሰፋ እንዲል ያደርገዋል የሚል አቋም አላቸው። “ይህን ግን ኢህአዴግ አልቀበልም ብሏል” ሲሉ በፖለቲካ ፓርቲዎች ድርድር የመገናኛ ብዙሃን ኮሚቴ አመራር አባሉ አቶ ዘመኑ ሞላ ለሰንደቅ ጋዜጣ ተናግረዋል። የመላው ኢትዮጵያ ዴሞክራሲ ፓርቲ (መኢዴፓ) ዋና ፀሐፊ እና በድርድሩ የሚዲያ ኮሚቴ አባል አቶ ዘመኑ አክለውም፤ “በተዋረድ የሚገኘው ምርጫ ቦርድ የተዋቀረው በምክር ቤት ወንበር ባላቸው ፓርቲዎች በመሆኑ ተቃዋሚዎች በአሁኑ የቦርድ አወቃቀር ተወካይ የላቸውም። ይህ አሰራር ጥሩ ባለመሆኑም በኮሚሽን ተዋቅሮ ተቃዋሚዎች በቦርዱ እንዲካተቱ ሲሉ 11ዱ ፓርቲዎች ጥያቄያቸውን አቅርበው ነበር። ኢህአዴግ አልቀበልም ያለው ይህን አማራጭ የመፍትሄ ሃሳብ ነው” በማለት ለሰንደቅ ጋዜጣ ተናግረዋል።


ድርድሩ ከመጀመሩ በፊት ገና በድርድሩ አካሄድ ላይ ያልተስማሙት መድረክና ሰማያዊ ራሳቸውን ከድርድሩ ውጭ ማድረጋቸው ይታወሳል።

ይምረጡ
(3 ሰዎች መርጠዋል)
294 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 1029 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us