137 ኢትዮጵያዊያን በቁጥጥር ስር ዋሉ

Wednesday, 08 November 2017 18:14

 

በሕገ-ወጥ መንገድ ወደ ሀገሪቱ ገብተዋል የተባሉ 137 ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በኬንያ ፖሊስ ቁጥጥር ስር ዋሉ።

ዥንዋ እንደዘገበው ባለፈው አርብ በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋሉት ኢትዮጵያዊኑ በሞያሌ በኩል ወደ ሀገሪቱ መግባታቸው ተረጋግጧል። ኢትዮጵያዊያኑ በሁለት ኬንያዊያን ሾፌሮች ታግዘው ወደ ሀገሪቱ እንደገቡ የገለፀው የሀገሪቱ ፖሊስ ኢትዮጵያዊኑ ወደ ደቡብ አፍሪካ እና ታንዛኒያ የመሻገር እቅድ እንዳላቸውም ገልጿል። የብካዮሌ ፖሊስ ጣቢያ አዛዥ ጆሴፍ ጊባንጂን ጠቅሶ የዜና አውታሩ እንዳስነበበው፤ ኢትዮጵያዊያኑ ወደ ፖሊስ ጣቢያ የተወሰዱ ሲሆን፤ ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ከመደረጉ በፊት ተገቢው የህግ ምርመራ ይደረግባቸዋል።

በተመሣሣይ ባለፈው የፈረንጆቹ ጥቅምት 6 ቀን ሌሎች 67 ህገ ወጥ ናቸው የተባሉ ኢትዮጵያዊያን በዚሁ አካባቢ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለው ነበር። በቁጥጥር ስር የዋሉት ኢትዮጵያዊያን ስራ ፍለጋ እንዲሁም ወደ ሌሎች ሀገራት ለመሸጋገር ወደ ሀገሪቱ እንደገቡ ተጠቅሷል። የሀገሪቱ ፖሊስ እና የስደተኞች ጉዳይ ቢሮ እንደገለፁትም በህገ ወጥ መንገድ ወደ ሀገሪቱ የሚገቡ ኢትዮጵያዊያን ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መጥቷል። በመቶዎች የሚቆጠሩ ወጣት ኢትዮጵያዊያን በየጊዜው በኬንያ እያቋረጡ ወደ ደቡብ አፍሪካ ስራ ፍለጋ እየተሰደዱ መሆናቸውን ዘገባው አመልክቷል። በፖሊስ ቁጥጥር ስራ የሚውሉትን ኢትዮጵያዊያን ጉዳይ ለመመርመር እና መፍትሄ ለመስጠትም ኢትዮጵያዊያኑ በስዋህሊ ወይም በእንግሊዝኛ ቋንቋ መግባባት አለመቻላቸው ችግር እየፈጠረ መሆኑን የሀገሪቱ ፖሊስ ገልጿል።

ይምረጡ
(2 ሰዎች መርጠዋል)
357 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 1038 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us