ሼህ አልአሙዲ ለሶማሌ ክልል ዕርዳታ ለገሱ

Wednesday, 03 May 2017 12:25

የሚድሮክ አትዮጵያ ሊቀመንበርና ባለሃብት የክብር ዶ/ር ሼህ ሙሐመድ ሁሴን ዓሊ አልአሙዲ ለሁለተኛ ጊዜ 35 ሚሊየን ብር የሚገመት የምግብ እህል እና የእንስሳት መኖ ዕርዳታ ለሶማሌ ክልል ሕዝብ ለገሱ።

ሼህ ሙሀመድ በሶማሌ ክልል በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች ዕርዳታ የሚውል 10ሺ ኩንታል ሩዝ፣ 10 ሺ ኩንታል በቆሎ፣ 10 ሺ ኩንታል አልፋ አልፋ የከብቶች መኖ ባለፈው ቅዳሜ ዕለት በተወካያቸው አማካይነት አስረክበዋል። በርክክቡ ሥነሥርዓት ላይ በክልሉ በኩል የሶማሌ ክልላዊ መንግሥት ርዕሰ መስተዳድር አቶ አብዲ መሐመድ ኦማር የተገኙ ሲሆን በኩባንያው በኩል የሼህ ሙሐመድ ተወካይ እንዲሁም የአካባቢው ሕዝብ ተገኝተዋል። አቶ አብዲ ፤ሼህ አልአሙዲ ላደረጉት ወገናዊ ድጋፍ በክልል ሕዝብ ስም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

የሼህ ሙሐመድ ተወካይ አቶ ኢሳያስ ከበደ በበኩላቸው ዕርዳታው ኢትዮጵያዊያን ያጋጠማቸውን የድርቅ አደጋ በራስ አቅም ለመመከት የሚያደርጉት ጥረት አካል ነው መሆኑን ተናግረዋል።

ሼህ ሙሐመድ በተመሳሳይ ሁኔታ በቅርቡ ለኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት 20 ሺ ኩንታል የምግብ እህል እና በ 20 ተሽከርካሪዎች የተጫነ አልፋ አልፋ የከብቶች መኖ መለገሳቸው የሚታወስ ነው።¾

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
663 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 108 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us