የሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ሁለት ኩባንያዎች ከኦዚ ኩባንያ ጋር በጋራ ለመሥራት ተስማሙ

Wednesday, 19 April 2017 12:32

 

በዶ/ር አረጋ ይርዳው የሚመራው የሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ አባል ካባንያዎች መካከል ሬይንቦ የመኪና ኪራይና የአስጎብኚ አገልግሎት ኃ/የተ/የግ/ማህበር እና የትራንስ ኔሽን ኤየርዌይስ ኃ/የተ/የግ/ማህበር፣ ከኦዚ ቢዝነስና ሆስፒታሊቲ ግሩፕ ጋር በቱሪዝም ዘርፍ አብሮ ለመስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ሰነድ ስምምነት ሰሞኑን አከናወኑ።

ሳር ቤት አካባቢ በሚገኘው የሬይንቦ ድርጅት ጽ/ቤት ባለፈው ረቡዕ ዕለት በተከናወነው የፊርማ ሥነሥርዓት ላይ በመገኘት ስምምነቱን የፈጸሙት በሬይንቦ በኩል ዋና ስራ አስኪያጁ አቶ ታፈሰ ሳህሌ፣ በትራንስ ኔሽን በኩል ካፒቴን ተፈሪ ኃይሌ፣ በኦዚ በኩል አቶ ቁምነገር ተከተል የኩባንያው ማኔጂንግ ዳይሬክተር ናቸው።

በሥነሥርዓቱ ላይ ተገኝተው ንግግር ካደረጉት እንግዶች መካከል የሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ቺፍ ኤግዚኪዩቲቭ ኦፊሰር ዶ/ር አረጋ ይርዳው በቅድሚያ የፊርማ ሥነሥርዓቱ ስለተካሄደበት የሳር ቤት ታሪካዊነት ማብራሪያ ሰጥተዋል። «ይህቺ የምንገኝባት የሳር ቤት በንጉሱ ዘመን በአካባቢው ከነበሩት አራት የሳር ቤቶች መካከል አንድዋ  ናት። እዚህ ግቢ ውስጥ ከመፍረስ የዳኑ ሁለት ቤቶች አሉ። ሌሎች ሁለቱ ፈርሰው አደባባይ ተሰርቶባቸዋል። እነዚህ ቤቶች ሰፈሩን ሳር ቤት ያስባሉ ታሪካዊ ቅርሶች ናቸው። ወደፊት እንዳይፈርሱ፣ ታሪካዊነታቸው እንዲጠበቅ እያደረግን ነው። በዚህ ረገድ እንድታግዙን እንፈልጋለን» ብለዋል።

በቱሪዝም ዘርፍ ሀገሪቷ ትልቅ ሐብት እያላት እስካሁን ድረስ አልተጠቀምንበትም ያሉት ዶ/ር አረጋ ይህን ለመለወጥ የሁላችንም ትብብር ያስፈልጋል፡፡ ተቀናጅቶ አብሮ ለመስራት መታሰቡ ጥሩ መሆኑንና የእኔ ስራ ይህን እንዲሳካ ማገዝ ነው ብለዋል። የክብር ዶ/ር ሼህ ሙሐመድ ሁሴን አሊ አልአሙዲ ለዘርፉ ዕድገት አቅማቸው የፈቀደውን ሁሉ እያደረጉ መሆኑን ያስታወሱት ዶ/ር አረጋ የአፍሪካ ህብረትን መቀመጫ ወደሊቢያ ለመውሰድ እነጋዳፊ በተንቀሳቀሱበት ወቅት አንዱ ምክንያታቸው የነበረው በቂ የትራንስፓርት አገልግሎት የለም የሚል በመሆኑ ሼህ ሙሐመድ ይህን ክፍተት ለመድፈን በሁለት ሳምንት ጊዜ ውስጥ 60 ማርቼዲስ ዘመናዊ መኪኖችን ከውጭ ሀገር ገዝተው ወደሀገር ውስጥ ማስገባታቸውንና መኪኖቹ እስካሁን ድረስ አገልግሎት እየሰጡ መሆኑን አስታውሰዋል። በተጨማሪም በሀገሪቱ የንግድ ሄሊኮፕተር አገልገሎት እንዲጀመር ለማድረግ 13 ዓመታት ያህል ጊዜ መፍጀቱን ተናግረው በአሁኑ ጊዜ የሄሊኮፕተር አገልግሎት በትራንስ በኩል እየተሰጠ መሆኑን ጠቁመዋል። በስፖርት ዘርፍ በቅርቡ ከግማሽ ቢሊየን ብር በላይ የፈጀ ስታዲየም በወልዲያ ከተማ መገንባቱንና ይህም ለዘርፉ ዕድገት የበኩሉን አስተዋጽኦ እንደሚያደርግ፣ ነገር ግን እስካሁን ምንም ዓይነት ጨዋታ እየተካሄደበት አለመሆኑን በመጥቀስ የምንሽከረከረው በአዲስ አበባ ብቻ እስከሆነ ድረስ ኢትዮጵያ አዲስ አበባ ሆና ትቀራለች፤ ወጣ ብሎ ክልሎች አካባቢ የስፖርት ቱሪዝምን ለማስፋፋት መንቀሳቀስ ያስፈልጋል ሲሉ መክረዋል።

አቶ ሰለሞን ታደሰ የኢትዮጵያ ቱሪዝም ድርጅት ዋና ስራ አስፈጻሚ በበኩላቸው ቱሪዝምን በተመለከተ በእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ልብ ውስጥ ኃይለኛ ፍላጎት፣ ቁጭት መኖሩን አስታውሰው ነገርግን ያለንን ሐብት በአግባቡ እየተጠቀምንበት አይደለም ብለዋል። ዘርፉን ለማሳደግ መንግሥት ብቻውን እንደማይችለው በመጥቀስ ሶስት ድርጅቶች አብረው ለመስራት ማቀዳቸው ትልቅ ምሳሌ የሚሆን መሆኑን ተናግረዋል። ቱሪዝምን ለማሳደግ የማይስ ወይም የስብሰባ ቱሪዝም እና የስፖርት ቱሪዝም መስፋፋት ይኖርበታል በማለት ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ አሳስበዋል።

 የሬይንቦ የመኪና ኪራይና የአስጎብኚ አገልግሎት ኃ/የተ/የግ/ማህበር ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ታፈሰ ሳህሌ በበኩላቸው ሬይንቦ ከመኪና ኪራይ አገልግሎት በተጨማሪ የሀገሪትዋን ቱሪዝም ለማሳደግ የራሱን ዕቅድ በመያዝ ሲንቀሳቀስ መቆየቱን ጠቅሰው እንደኦዚ ካሉ ድርጅት ጋር በጋራ መስራቱ ጥረቱን ለማሳደግ ይረዳዋል በማለት ብለዋል።

አቶ ቁምነገር ተከተል የኦዚ ቢዝነስና ሆስፒታሊቲ ግሩፕ ማኔጂንግ ዳይሬክተር በበኩላቸው በጋራ አብረን እንስራ ብለን ያቀድነው ቱሪዝም የአንድ ሰው ኃላፊነት አለመሆኑን በመረዳት ነው ብለዋል። በስብሰባ ቱሪዝም እንደተለመደው ቱሪስቶችን ሳይቶችን ከማስጎብኘት፣ ባህልን ከማስተዋወቅ ባለፈ አቅም ፈጥረን ለመንቀሳቀስ በመፈለጋችን ነው ሲሉ ተናጋረው በዘርፉ ሌሎች የደረሱበት ለመድረስ ትብብሩ አስፈላጊ መሆኑን አስረድተዋል።¾

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
554 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 103 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us