ሼክ ሙሐመድ ሁሴን ዓሊ አልአሙዲ በኦሮሚያ ክልል በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች ዕርዳታ ለገሱ

Wednesday, 12 April 2017 12:01

የሚድሮክ ኢትዮጵያ ሊቀመንበር የክብር ዶ/ር ሼክ ሙሐመድ ሁሴን አሊ አልአሙዲ በኦሮሚያ ክልል በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች የሚውል 20 ሺህ ኩንታል የእህል ድጋፍ በቅርቡ ማድረጋቸው ተሰማ።

በተጨማሪም ለእንስሳት መኖ የሚውል 20 ተሽከርካሪ አልፋ አልፋ የተባለ የእንስሳት መኖ መለገሳቸውን የኦሮሚያ ክልል የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ሀላፊ አቶ አዲሱ አረጋ አስታውቀዋል።

ሼክ ሙሐመድ  በክልሉ በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች ላደረጉት ድጋፍም አቶ አዲሱ በክልሉ መንግስት ስም ምስጋናቸውን ማቅረባቸውን የዜናው ምንጭ ራዲዮ ፋና ዘግቧል።

ሼክ ሙሐመድ ከአንድ ወር በፊት በአዲስ አበባ በቆሼ አካባቢ በቆሻሻ መደርመስ አደጋ ለደረሰባቸው ወገኖች የ40 ሚሊየን ብር የገንዘብ ድጋፍ ማድረጋቸው አይዘነጋም።¾

ይምረጡ
(3 ሰዎች መርጠዋል)
638 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 105 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us