ዩኒቲ ዩኒቨርስቲ ከዳሸን ባንክ ጋር የአቅም ግንባታ ሥልጠና ስምምነት ፈፀመ

Wednesday, 22 June 2016 12:02

-    በመቻሬ ህፃናት ማቆያ የሚያድጉ ህፃናት እስከዩኒቨርስቲ

የሚዘልቅ የነፃ ትምህርት ዕድል አገኙ

 

ዩኒቲ ዩኒቨርስቲ እና ዳሸን ባንክ በአቅም ግንባታ ዙሪያ አብረው ለመሥራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ሰነድ ስምምነት ሰኔ 1 ቀን 2008 ዓ.ም አከናወኑ።

ስምምነቱ የዳሸን ባንክ አ/ማ ሠራተኞች እና ሥራ አመራሮች በዩኒቲ ዩኒቨርስቲ አጫጭር የሙያ ሥልጠናዎች እንዲያገኙ የሚያስችል ነው። በስምምነቱ መሠረት ዘጠኝ በሚደርስ የሙያ ዘርፎች ማለትም በደንበኞች አያያዝ፣ በፕሮጀክት ማነጅመንት፣ በሰክሬቴሪያል ሳይንስና ኦፊስ ማኔጅመንት፣ በማቴሪያል ማኔጅመንት፣ በቼንጅ ማኔጅመንት፣ በኮርፖሬት ገቨርናንስ፣ በማርኬቲንግ ማኔጅመንትና በመሳሰሉት ሙያዎች የዳሸን ባንክ ሠራተኞች አጫጭር ሥልጠናዎች እንዲያገኙ ይደረጋል።

ስምምነቱን አስመልክቶ ዶ/ር ቡቴ ጉቴ የዩኒቲ ዩኒቨርስቲ ምክትል ፕሬዚዳንት ለሰንደቅ ጋዜጣ በሰጡት ማብራሪያ በዩኒቲ ዩኒቨርስቲ እና በዳሸን ባንክ መካከል የአቅም ግንባታ ሥልጠና ትብብር ከስምምነቱ በፊት ቀደም ብሎ የተጀመረ እንደነበርና ባለፈው አንድ ዓመት ጊዜ ወደ አንድ ሺህ የሚጠጉ የዳሸን ባንክ ሠራተኞች የተለያዩ ሥልጠናዎችን እንዲያገኙ መደረጉን ጠቁመዋል። የአሁኑ ስምምነት ሁለቱ አካላት ትብብራቸውን የበለጠ እንዲያጠናክሩ ይረዳቸዋል ብለዋል።

ሥልጠናው ባንኩ ለህብረተሰቡ የሚሰጠውን አገልግሎት በከፍተኛ ደረጃ እንዲያሳድግና ተወዳዳሪነቱ እንዲጨምር እንደሚረዳውም ከዶ/ር ቡቱ ገለፃ ለመረዳት ተችሏል።

በሚድሮክ ኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ዋና መ/ቤት በተካሄደው የፊርማ ሥነሥርዓት ላይ ተገኝተው ስምምነቱን የፈረሙት የዳሸን ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ አስፋው ዓለሙ እና የሚድሮክ ኢትዮጵያ ቺፍ ኤግዚኪዩቲቭ ኦፊሰር እና የዩኒቲ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር አረጋ ይርዳው ናቸው።

በተያያዘ ዜና የሚድሮክ ኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ያዘጋጀውን በአገር አቀፍ ደረጃ በአርአያነቱ የሚጠቀሰው መቻሬ ኮርፖሬት ሴንተር ውስጥ የሚገኘው የሕፃናት ማቆያ ሥራ የጀመረበት ሁለተኛ ዓመት ሰኔ 3 ቀን 2008 ዓ.ም ተከብሮ ውሏል።

በአሁኑ ወቅት በሕፃናት ማቆያው የሚገኙ 18 ሕፃናት በዕለቱ ለዶ/ር አረጋ ይርዳው የእቅፍ አበባ በማበርከት የእንኳን ደህና መጡ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ዶ/ር አረጋ ይርዳው በሥነሥርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር የመቻሬ የሕፃናት ማቆያ ማዕከሉ የሚያድጉ ሕፃናት ወላጆቻቸው በሥራ ላይ እስካሉ ድረስ ከማቆያው እስከ ዩኒቨርስቲ የነፃ ትምህርት ዕድል ለመስጠት ቃል ከመግባታቸው በተጨማሪም ሕጻናቱን የሚንከባከቡ የማዕከሉ ሠራተኞች የ20 በመቶ የደመወዝ ጭማሪ በማድረግ አበረታተዋቸዋል።

የሕፃናት ማቆያው ማዕከሉ የሕጻናት ማረፊያ፣ መጫወቻ፣ መመገቢያ፣ የመፀዳጃ እና የመታጠቢያ አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን የህጻናቱ ወላጆች በፈረቃ በመግባት ሕጻናቱን እነደሚንከባከቡ ታውቋል።

የሕፃናት ማቆያ ማዕከሉ መከፈቱ ሠራተኞቹ ሕፃናት ልጆቻቸውን ወደማቆያው በመውሰድ ሥራቸውን ተረጋግተው እንዲሰሩና በአቅራቢያ ሆነው ልጆቻቸውን እንዲከባከቡ ምቹ ሁኔታ መፍጠሩም ታውቋል።

ይምረጡ
(3 ሰዎች መርጠዋል)
941 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 1057 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us