ሼህ ሙሐመድ ባበረከቱት የበጎ አድራጎት ሥራ ተሸለሙ

Wednesday, 15 June 2016 12:23

 

በቀዳማዊት እመቤት ወ/ሮ ሮማን ተስፋዬ የሚመራው የእናት ወግ የበጎ አድራጎት ማኅበር በአዲስ አበባ በትምህርት ቤቶች ለሚያከናውነው የተማሪዎች ምገባ ፕሮግራም ድጋፍ ካደረጉ ተቋማትና ግለሰቦች መካከል የክብር ዶ/ር ሼህ ሙሐመድ ሁሴን ዓሊ አልአሙዲ አንዱ አድርጎ ሸለመ።

ማኅበሩ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ከትላንትበስቲያ ባካሄደው የእውቅና አሰጣጥ ፕሮግራም ላይ በሀገር ውስጥና በውጪ ሀገር የሚገኙ 52 ተቋማትና ግለሰቦችን ሸልሟል።

በአዲስ አበባ ውስጥ በሚገኙ ት/ቤቶች ከሚማሩ ተማሪዎች መካከል በምግብ እጥረት የሚቸገሩ ተማሪዎች መኖራቸው ተረጋግጦ ከአንድ ዓመት በፊት በቀን ሁለት ጊዜ የምገባ ፕሮግራም ተጀምሯል። የሚድሮክ ኢትዮጵያ ሊቀመንበርና ባለሀብት የክብር ዶ/ር ሼህ ሙሐመድ ሁሴን ዓሊ አልአሙዲ የእናት ወግ የበጎ አድራጎት ድርጅት የቁርስና የምሣ የምገባ ፕሮግራም ከሚያደርግላቸው 20ሺህ ተማሪዎች መካከል 10ሺህ ያህሉን ወጪ በመሸፈን ላደረጉት የላቀ አስተዋፅኦ ከወ/ሮ ሮማን እጅ የተዘጋጀላቸው የምስክር ወረቀት ወስደዋል።n

ይምረጡ
(3 ሰዎች መርጠዋል)
959 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 105 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us