ሼክ ሙሐመድ 16 ሚሊዮን ብር ለሜቄዶኒያ ለገሱ

Wednesday, 04 May 2016 12:53

“በለገሱን አንቡላንስ ከ800 በላይ አረጋዊያንን ከጎዳና ላይ ማንሳት ችለናል”

አቶ ቢኒያም በለጠ

የመቄዶኒያ ማዕከል መስራችና ስራአስኪያጅ

 

የክብር ዶ/ር ሼክ ሙሐመድ ሁሴን አሊ አል አሙዲ የትንሳኤን በዓል ምክንያት በማድረግ ለመቄዶንያ የአረጋዊያንና የአእምሮ ሕሙማን መርጃ ማዕከል ሰሞኑን የ16 ሚሊዮን ብር ስጦታ ማበርከታቸውን ማዕከሉ አስታወቀ።

የመቄዶኒያ ማዕከል መስራችና ስራአስኪያጅ አቶ ቢኒያም በለጠ ለሰንደቅ ጋዜጣ እንደተናገሩት፣ “ሼክ ሙሐመድ የትንሳኤን በዓል ምክንያት በማድረግ ለማዕከላችን የ16 ሚሊዮን ብር በስጦታ አበርክተውልናል። ከዚህ በፊትም በገንዘብም በአይነትም ብዙ ድጋፎች አድርገውልናል። ለምሳሌ በእሳቸው በተበረከተልን አምቡላንሶች ከ800 በላይ አረጋዊያንን ከጎዳና ላይ ማንሳት ችለናል። የእሳቸውን እገዛ ባናገኝ አረጋዊያንን ከወደቁበት ለማንሳት አስቸጋሪ ይሆንብን ነበር።ሼክ ሙሐመድ ከአሁኑ ድጋፋቸው በተጨማሪ ከዚህ ቀደምም በተመሳሳይ ሁኔታ ባስተላለፉት መመሪያ የሞሃ የለስላሳ መጠጦች ፋብሪካ፣ ዳሽን ባንክ፣ ኤልፎራ፣ አዲስ ጎማ፣ ኒያላ ሞተር፣ ደርባ ሲሚንቶ እና ኩዊንስ ሱፐር ማርኬት፣ ዩኒቲ ዩኒቨርስቲ፣ አንሊሚትድ ፓኪንግ ፋብሪካ፣ አዲስ ፓርክ፣ የላይኛው አዋሽ አግሮ ኢንዱስትሪ እና ሚድሮክ ኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ግሩፕ በገንዘብ እና በዓይነት ከ10 ሚሊዮን ብር በላይ ረድተውናል” ብለዋል።

“ከሼክ ሙሐመድ ጋር በአካል ተገናኝታችሁ መወያየታችሁ ይታወሳል። ውይይታችሁ ምን ላይ ያተኮረ ነበር?” ተብሎ ለቀረበለት ጥያቄ ቢኒያም ሲመልስ፣ “ አብዛኛውን ጊዜ እገዛ ፈልገን በተለያዩ ቦታዎች በመሄድ በር እናንኳኳለን። እሳቸው ግን ጠርተውን ስንወያይ ምን ላግዛችሁ? ነበር ያሉን። ስለሜቄዶኒያ ብዙ ነገር ያውቃሉ። የገረመኝ ግን ከለገሱት በላይ፣ ለመለገስ ያላቸው እምነትና ፍላጎት እጅግ ልብ የሚነካ ነው። ሃሳባቸው በጣም ሰፊ መሆኑን ተረድቻለሁ። ለየት ያለብኝ ለሚያደርጉት ነገር ምስጋና አይፈልጉም። ማድረጋቸውም እንዲነገር አይፈልጉም። በውይይቶቻችን መካከል ፈጣሪያችሁን ብቻ አመስግኑ ነው የሚሉት። ከዚህ አባባላቸው የተረዳሁት ለፈጣሪያቸው ሲሉ ብቻ ነው ልገሳ የሚያደርጉት። አንድም የተለየ ፍላጎት እንደሌላቸው ተረድቻለሁ። ሲያናግሩ ያላቸው ትህትህ በአብዛኛው ባለጸጎች ከሚባሉት የምትጠብቀው አይነት አይደለም። ሲበዛ ትሁት ናቸው” ብሏል።

ባለሃብቱን በመወከል የ16 ሚሊየን ብር የገንዘብ ስጦታውን የሰጡት የሞሃ ለስላሳ መጠጦች ኢንዱስትሪ ሥራ አስኪያጅ አቶ ጌታቸው ቢርቦ “የመቄዶኒያ ማዕከል እያደረገ ያለውን እጅግ የላቀ የሰብዓዊ ተግባር ሼክ ሙሐመድ እንደሚያደንቁ በመግለጽ ማዕከሉ ከምንም ጊዜው በላይ በአሁኑ ወቅት ከሕብረተሰቡ ከፍተኛ የሆነ እገዛ የሚያስፈልገው መሆኑን በመጠቆም ማዕከሉ በቀጣይም የባለሃብቱ እርዳታ እንደማይለየው” ቃል ገብተዋል። ይህ ድጋፍ ከሼክ ሙሐመድ ኩባንያዎች ማለትም ከሞሃ ለስላሳ 6 ሚሊየን ብር፣ ከሚድሮክ ኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ግሩፕ 10 ሚሊየን ብር የተለገሰ መሆኑ በርክክብ ሥነሥርዓቱ ወቅት ተገልጿል።

በአሁን ሰዓት የመቄዶንያ የአረጋዊያንና የአእምሮ ሕሙማን መረጃ ማዕከል አንድ ሺህ ሰዎችን እየረዳ ይገኛል። በየወሩ ለአረጋዊያንና ለአእምሮ ሕሙማን የምግብ ፍጆታ ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ያደርጋል። አዲስ ለሚያስገነባው ማዕከል 300 ሚሊዮን ብር ያስፈልገዋል። ስለዚህም አቶ ቢኒያም እስከ አሁን ሕብረተሰቡ ላደረገው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበው፣ የተጀመረው እርዳታ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ለኢትዮጵያ ሕዝብ ጥሪ አቅርበዋል።n

ይምረጡ
(3 ሰዎች መርጠዋል)
1142 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 107 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us