የህዳሴውን ግድብ ለማጥቃት ተሰናድተው ነበር የተባሉ የቤንሻንጉል ጉሙዝ ተወላጆች ተከሰሱ

Thursday, 16 October 2014 12:41

የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልልን በኃይል ከፌዴሬሽኑ ለመገንጠል አሲረው፤ በኤርትራ የፖለቲካና የጦር ስልጠና በመውሰድ፣ አባላትን በመመልመልና የተደራጀ ጥቃት በመሰንዘር የአባይን ግድብ ሥራ ለማስተጓጎል ሲንቀሳቀሱ ነበር በሚል የፌዴራል ዐቃቤ ሕግ በስድስት የክልሉ ተወላጆች ላይ የሽብር ክስ መሰረተ።

በትናንትናው ዕለት (ጥቅምት 4 ቀን 2007 ዓ.ም) በፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት ክሳቸውን ቀርበው ያደመጡት ተጠርጣሪዎች 1ኛ አብዱልከሪም አብዱልሰመድ፣ 2ኛ ሀዋጃ ሚነላ፣ 3ኛ ኢሳቅ አብራሃም፣ 4ኛ አጄል ጃባላ፤ 5ኛ አብዱ ሀሚዝ ፈረንሳይ እና 6ኛው ደግሞ ፈተልሙላ አጣሂር ናቸው።

እንደዐቃቤ ሕግ የክስ ዝርዝር ከሆነ፤ ተከሳሾቹ በዋና ወንጀል አድራጊነት ተካፋይ በመሆን በቀጥታ እንዲሁም በመላ ሃሳባቸውና አድራጎታቸው በወንጀል ድርጊቱና በሚሰጠው ውጤት ሙሉ ተካፋይ በመሆን የሽብርተኛ ደርጅት አባል ሆነው፤ አባላትን በመመልመል፤ የጦርና የፖለቲካ ስልጠና ኤርትራ ድረስ በመሄድ በመውሰድና ተመልሰው በክልሉ የሚሊሻ ኃይሎች ጋር ግጭት በመፍጠር ታላቁ የህዳሴ ግድብን ስራ ለማስተጓጎል አሲረዋል የሚል ክስ አቅርቦባቸዋል። ለዚህም ለሽብር ተግባራቸው በርካታ አይነትና መጠን ያላቸውን የጦር መሳሪያዎች ስለመጠቀማቸው ዐቃቤ ሕግ በክስ ዝርዝሩ ያትታል።

በአጠቃላይም ይላል የዐቃቤ ሕግ የክስ መዝገብ፤ ተከሳሾች በሽብርተኛ ድርጅት ውስጥ አባል በመሆን፤ ስልጠና በመውሰድ፤ የሽብር ተልዕኮ በመቀበልና የሽብር ድርጅቱን የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች በመታጠቅ ስልጠና ከወሰዱበት ሀገር ወደኢትዮጵያ ለመግባት በጉዞ ላይ እያሉ በቁጥጥር ስር በማዋላቸው ለዋና ወንጀል አድራጊነት ተካፋይ በመሆን በፈፀሙት የሽብር ድርጅት ውስጥ የመሳተፍ ወንጀል ተከሰዋል ይላል።

ለዚህም ዐቃቤ ሕግ በርካታ የሰውና የሰነድ ማስረጃዎችን አጣቅሶ ከክስ ቻርጁ ጋር ያቀረበ ሲሆን፤ ትናንት ክሱ የተነበበላቸው ስድስት ተጠርጣሪዎችም በተከላካይ ጠበቃቸው በኩል የክስ መቃወሚያ ካላቸው ለመስማት ለጥቅምት 25 ቀን 2007 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

በተያያዘ ዜና “በመንግስት ህግ አንተዳደርም፤ በቁርአን የሚመራ መንግስት እንመሰርታለን፤ ለመንግስት ግብር መክፈል የለብንምና በመንግስት አገልግሎት ላይ መሳተፍ የለብንም” በሚል የአድማ ስምምነት በማድረግ ከ1995 ዓ.ም ጀምሮ “ሙስሊም ጅማ” የተሰኘ የሽብር ቡድን አቋቁመው እስላማዊ መንግስትን ለማቋቋም ሲንቀሳቀሱ ነበር ሲል የፌዴራል ዐቃቤ ሕግ የዘረዘራቸው ስምነት ግለሰቦች ትናንት ማክሰኞ (ጥቅምት 4 ቀን 2007 ዓ.ም) በፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት ቀርበው ክስ ተመሰረተባቸው። ከሳሾቹ ሼህ መንሱር አባቡር፣ መሀመድ ኢሚባ፣ አወል አባሜንጫ፣ አብዱላዜዝ አባዝናብ፣ ጣሂር አባኑራ፣ ሳበት ከድር፣ መሀመድ አባንሮ እና አብዱ ሁሴን የተባሉ የጅማ ከተማ ነዋሪዎች ናቸው ይላል ዐቃቤ ሕግ።

ተከሳሾቹ አባላትን ለመመልመል፣ የጦር መሣሪያዎችን በመታጠቅና ኃይላቸውን በማደራጀት በጅማ ዞን ሸቤ እና ዴዶ በተሰኙ ወረዳዎች እንዲሁም አዋሳኝ አካባቢዎች ላይ በሚመላለሱ የህዝብ ተሽከርካሪዎን በማስቆምና ግድያና ዘረፋ በመፈፀም ለሽብር ቡድኑ ተግባር ማስፈፀሚያ ገንዘብ ሲሰበሰቡ ነበር የሚል ክስ ቀርቦባቸዋል።

ግለሰቦቹ በእስልምና ሕግ የሚተዳደር ሀገር እንመሰርታለን በሚል ግድያና ዝርፊያ በመፈፀም ለሽብር ቡድኑን የጦር መሳሪያ አግዘዋል፤ በተለይም 1ኛው ተከሳሽ ሼህ በድሩ አባቡር በ2001 ዓ.ም ሀቢብ ከድር ከተባለ ህዳር 2006 ዓ.ም በጅማ ዞን ሸቤ የውጪ ሀገር ዜጋን በመግደል፣ 30 ሞባይሎችን እና በርካታ ገንዘብ ለመዝረፍ በጦር መሳሪያ የታገዘ ጥቃት ፈፅመዋል። ከዚህም ባሻገር ከዴዶ ወደጅማ የሚጓዝ የህዝብ ማመላለሻን በማስቆም አንድ የፖሊስ አባልን ጨምሮ ሶስት ግለሰቦችን በመግደል ዝርፊያ ፈፅመዋል ሲል ዐቃቤ ሕግ በክሱ ያትታል።

በስተመጨረሻም የሽብር ቡድኑ አባላት እየዘረፉ መልካ አቻኖ በተሰኘ ጫካ ውስጥ መሽገው ከደቡብ ክልል ወደጅማ ይጓዝ የነበረ መኪና ላይ ጥቃት መሰንዘራቸውንና የሞት የአካልና የንብረት ጉዳት ስለማድረሳቸው ያትታል። ይህ የሽብር ቡድን ጅማ ከተማ ቲሻየር በሚሰኝ ቀበሌ ተሸሽገው እጅ እንዲሰጡ ቢጠየቁም እምቢ በማለታቸው በተደረገው የተኩስ ልውውጥ የአንድ ፖሊስ አባል ህይወት አልፏል፤ በሌላም ላይ የመቁሰል አደጋ ፈጥሯል ብሏል።

በትናንትናው እለት በፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት ቀርበው የተመሰረተባቸው ክሳቸውን ያደመጡት ተጠርጣሪዎቹ በክሱ ላይ ያላቸውን ተቃውሞ ለመስማት ለጥቅምት 24 ቀን 2007 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷቸዋል።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
1206 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 1047 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us