ዳሸን ባንክና ኢታሶልዩሽንስ የታክሲ ክፍያን በካርድ ለመስጠት ተስማሙ

Friday, 12 January 2018 16:45

 

ዳሸን ባንክ አክስዮን ማህበር እና የሜትር ታክሲ አገልግሎት የሚሰጠው ኢታ ሶልዩሽንስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር (ETTA Solutions PLC) ለሜትር ታክሲ ተጠቃሚ ደንበኞቻቸው በጋራ ጥምርታ ካርድ (Co-Branded Cards) የኮርፖሬትና የቅድመ ክፍያ ካርድ አገልግሎትን በጋራ ለመስጠት ሥምምነት ተፈራረሙ። በዚሁ ገለፃቸውም አገልግሎት ሰጪው ኩባንያ ለሰጠው አገልግሎት ከሚቆርጠው ገንዘብ ውጪ ባንኩ ደንበኞቹ በኢታ የታክሲ አገልግሎት ሲጠቀሙ የሚጠይቀው ወይንም የሚቆርጠው ተጨማሪ የአገልግሎት ክፍያ አለመኖሩን ጨምረው ገልፀዋል። ኢታ ሶልዩሽንስ ፈላጊና ተፈላጊ ደንበኞቹን ለማገናኘት በራሱ አፕልኬሽን፣ በኢንተርኔት፣ በፌስቡክና በቴሌግራም ቴክኖሎጂዎች የሚጠቀም መሆኑ ታውቋል።

 

 ኢታ ሶልዩሽንስ ተደራሽነቱን ለማስፋትና አስተማማኝ ለማድረግ ከኢንተርኔት አገልግሎቱ በተጨማሪ በ8707 የጥሪ ማዕከሉ አማካኝነት አገልግሎት እየሰጠ የሚገኝ መሆኑ ተመልክቷል። አንድ የታክሲ ተጠቃሚ ደንበኛ ይሄንን አገልግሎት ሲጠቀም ታክሲውን ካሉት የቴክኖሎጂ አማራጮች በአንዱ ታክሲውን ከጠራ በኋላ ለአገልግሎቱ የሚጠየቀውን ክፍያ መጠን፤ እንደዚሁም ታክሲው ደንበኛው ያለበት ቦታ እስኪደርስ ድረስ ያለውን ሂደት መከታተል የሚያስችለው መሆኑም ታውቋል።

 

 ይህ የሁለቱ ኩባንያዎች የአገልግሎት ጥምረት የኢታ ሜትር ታክሲ ተጠቃሚ ደንበኞች ያለምንም የጥሬ ገንዘብ ንክኪ በካርድ አማካኝነት ብቻ ተጠቅመው የታክሲ አገልግሎት ክፍያቸውን እንዲፈፅሙ የሚያስችል ነው። የዳሸን ባንክ አክስዮን ማህበር ፕሬዝዳንት አቶ አስፋው  አለሙና የኢትዮጵያ ታክሲዎች ሶልዩሽንስ (ETTA) መስራችና ማኔጂግ ዳይሬክተር አቶ ተመስገን ገብረ ህይወት የአገልግሎቱን መጀመር ታህሳስ 25 ቀን 2010 ዓ.ም በሸራተን ሆቴል በተካሄደ ሥነ ሥርዓት በጋራ አብስረዋል።

 

አቶ ተመስገን ድርጅታቸው እየሰጠ ባለው አገልግሎት በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገራት የተለያዩ ሽልማቶችን ያገኘ መሆኑን በእለቱ በሰጡት ማብራሪያ አመልክተዋል። በዚህም ድርጅቱ እውን ከሆነበት ከግንቦት 2008 ዓ.ም ጀምሮ ሁለት የሀገር ውስጥና ከሁለት በላይ የውጭ ሽልማቶችን አግኝቷል ተብሏል።

 

 በአፍሪካ በመልካም የደንበኞች መስተንግዶና በትራንስፖርት ኢንዱስትሪው ዘርፍ ድርጅቶችን መርጦ ደረጃ የሚሰጠው ባንክ ኤንድ ኢንተርፐርነርስ መጋዚን ኢታ ሶልዩስን ኩባንያን  ምርጥ ብሎ ከለያቸው መቶ ድርጅቶች ውስጥ የ52ኛ ደረጃ የሰጠው መሆኑን ኃላፊው ጨምረው ገልፀዋል።

 

 በቀጣይም በአፍሪካ ያሉ አዲስ ጀማሪ ቢዝነሶችን የሚያበረታታውና ሰፒድ አፍሪካ በመባል የሚታወቀው ድርጅት በጥር ወር ላይ  ኢታን ከምስራቅ አፍሪካ በአንደኝነት የመረጠው በመሆኑ ወደ ሌጎስ ናይጄሪያ በመጓዝ ሽልማቱን የሚረከብ መሆኑን አቶ ተመስገን ጨምረው አመልክተዋል።

 

ዳሸን ባንክ የመጀመሪያው የፕላስቲክ ካርድን ጥቅም ላይ ያዋለ ባንክ መሆኑን የገለፁት አቶ አስፋው በበኩላቸው፤ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ባንኩ በዓለማችን ካሉ አራት ታላላቅ የካርድ አገልግሎት ከሚሰጡ ኩባንያዎች ጋር በጋራ እየሰራ መሆኑን  አመልክተዋል። እነዚህም ካርዶች ኤሜሪካን ኤክስፕረስ ካርድ፣ ማስተር ካርድ፣ ቪዛ ካርድን እና ቻይና ዩኒየን ፔይ ካርድን መሆናቸውን አቶ አስፋው ጨምረው አመልክተዋል። ባንኩ ካሽ አልባ ግብይትን የበለጠ ለማበረታታት የዘመኑን ቴክኖሎጂ በመጠቀም ደንበኞቹ ባንክ መሄድ ሳያስፈልጋቸው ክፍያ የሚፈፅሙበት ስርዓትን በተከታታይ እየተገበረ መሆኑም ተመልክቷል።

 

 እንደ አቶ አስፋው ገለፃ ባንኩ ከዚሁ ጋር በተያያዘ እየሰራ ባለው ሥራ የዲኤስ ቲቪ ተጠቃሚዎች የአገልግሎት ክፍያቸውን በሞባይል ባንኪንግ አማካኝነት መፈፀም እንዲያስችላቸው፤ እንደዚሁም ደንበኞች የአውሮፕላን ትኬትን በሞባይል ባንኪንኪግ አማካኝነት መግዛት እንዲችሉ ዳሸን ባንክ፤ ከዲኤስ ቲቪ እና ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር ሥምምነት ላይ ደርሶ ወደ ሥራ ገብቷል።

ባንኩከኢታበተጨማሪበቀጣይምበመጪዎቹሳምንታትወይንምወራትውስጥከሌሎችየንግድተቋማትጋርበጋራየሚሰራበትንየጋራየካርድክፍያሥርዓትን (Co-branding) የሚጀምርመሆኑንፕሬዝዳንቱጨምረውገልፀዋል።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
96 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 942 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us