ኤልፎራ ጥራቱ የተጠበቀ የዶሮ ምርቶችን የሚያቀርብባቸውን ጣቢያዎች ቁጥር አሳደገ

Wednesday, 07 September 2016 13:37

 

በሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ኩባንያዎች አንዱ የሆነው ኤልፎራ አግሮ ኢንዱስትሪ ኃ/የተ/የግ/ማ ከመጪው የዘመን መለወጫ በዓል ጋር ተያይዞ ለህብረተሰቡ ስለሚያቀርበው የዶሮ ምርት በተመለከተ ከዋና ሥራአስኪያጁ ከአቶ አንበሴ አሥራት እና ከዶሮ እርባታ የህክምናና ጥራት ቁጥጥር ሥራአስኪያጅ ዶ/ር ዳንኤል ፈረደ ጋር ያደረግነው አጠር ያለ የቃለምልልስ ቆይታ እንደሚከተለው ቀርቧል።

ሰንደቅ፡- ኤልፎራ የተሠማራባቸውን የሥራ መስኮች ቢያስታውሱኝ?

አቶ አንበሴ፡-  ኤልፎራ በሶስት ዋና ዋና የሥራ ዘርፎች ላይ የተሠማራ ትልቅ ኩባንያ ነው። አንደኛው በዘመናዊ እርሻ ላይ የሚያደርገው እንቅስቃሴ ነው። ሌላኛው በዶሮ እርባታ፣ በሶስተኛ በሥጋ ኤክስፖርት ዘርፍ ይሠራል። በተለይ እርሻዎችን ስንመለከት በጣም ሰፋፊ ናቸው። ባሉን እርሻዎች ላይ ሰብል ከማምረት በተጨማሪ ዘር በማባዛት በአካባቢው በሚገኝ ምርጥ ዘር ድርጅት አማካይነት ለገበሬው እንዲዳረስ ይደረጋል።

የዶሮ እርባታን በተመለከተ ኮመርሻል የሆነ የዶሮ እርባታ እንዲሁም በደብረ ዘይት፣ በመተሀራ፣ በኮምቦልቻና በመልጌ ወንዶ የሥጋ ማቀነባበሪያ ፋብሪካዎች አሉን። በተለይ በደብረዘይት በኤክስፖርት ሥጋ ምርት ላይ ያተኮረ ነው። ከኤክስፖርቱ በተጨማሪ በሀገር ውስጥ ለሚገኙ ዓለም አቀፍ ሆቴሎች፣ ዩኒቨርስቲዎች ሌሎች ተቋማት ምርቶቻችንን እናከፋፍላለን። በአሁኑ ሰዓት እርሻዎቻችን ዘመናዊ ለማድረግና የዶሮ እርባታውን ለማሳደግ ትልልቅ ፕሮጀክቶች ተቀርፀው እየሰራን  ነው። ከእርሻው በተጨማሪ የቢሾፍቱ ዶሮ እርባታ ድርጅታችን ለኅብረተሰቡ የዶሮዎችንና የእንቁላል ምርት ሲያቀርብ ከ20 ዓመታት በላይ ሆኖታል። ሁልጊዜ በአዲስ ዓመት፣ በገና እና በፋሲካ በዓላትን ለኀብረተሰቡ ዶሮዎችን  እናቀርባለን። እነኚህን ዶሮዎችን የምናቀርበው ከውጪ የምናስገባቸውን ጫጩቶች በማሳደግ ነው። ይህንን ስናቀርብ ከምናስመጣበት ቦታ ወደኢትዮጵያ ለማስገባት የእንስሳትና ዓሳ ሐብት ሚኒስቴር ፍቃድ እንወስዳለን። በሁለተኛ ደረጃ አቅራቢው ካምፓኒ ያለበት ሀገር ዓለም አቀፍ ሠርተፊኬት ይሰጠናል። የሀገር ውስጥ ፈቃዱንና ዓለምአቀፍ ሠርተፊኬቱን ካገኘን በኋላ ዶሮዎቹ ወደ ሀገር ውስጥ ይገባሉ።

ሰንደቅ፡- ዶሮዎቹ ወደእርባታ ማዕከል ከገቡ በኋላ ጤንነታቸውን በተመለከተ የምታደርጉትን ክትትል ቢያስረዱን?

አቶ አንበሴ፡-  ዶሮዎቹ ቢሾፍቱ ወደሚገኘው ድርጅታችን ከገቡ በኋላ በእንስሳት ህክምና የተመረቁ ባለሙያዎች ይረከቡና ከዚያ ቀን ጀምሮ ጤንነታቸውን፣ አመጋገባቸውን እየተከታተሉ ለኅብረተሰቡ እስከሚደርሱበት ጊዜ ድረስ ተገቢውን ክትትልና ድጋፍ ያደርጋሉ።

ሰንደቅ፡- የሽያጩ ሁኔታስ?

አቶ አንበሴ፡- እነዚህ ዶሮዎች ቀደም ሲል በተወሰኑ ጣቢያዎች ለገበያ እናቀርብ ነበር። አሁን ግን ለሕዝቡ ብዛትና ፍላጎት ማደግ ጋር ተያይዞ ወደ 19 የሽያጭ ጣቢዎች በአዲስ አበባ ብቻ ተከፍተው በመሸጫ ሰነድ ወደኅብረተሰቡ እንዲደርሱ ተገቢውን ዝግጅት አድርገናል። ይሄ ሁለት ጥቅም አለው። አንደኛው ለኅብረተሰቡ ጤንነታቸው የተጠበቁ ዶሮዎችን የማቅረብ፣ በሁለተኛ ደረጃ ኅብረተሰቡ በሚኖርበት አካባቢ ዶሮዎችን እንዲያገኝ የማድረግ ሥራ እየተከናወነ ነው። በዚህ ሁኔታ ኩባንያችን በጣም የታወቀበት በበዓላት ወቅት በተመጣጣኝ ዋጋ፣ ጥራት ያላቸው የዶሮ ምርቶችን ለኅብረተሰቡ በማቅረብ ትልቅ ቦታ ያለው ነው።

ዶ/ር ዳንኤል፡-  በዚህ ላይ የማቀርበው ተጨማሪ ሃሳብ፤ዶሮዎችን የማርባት ሥራችን ያለው ክትትል በጣም የተጠናከረ መሆኑን ነው። እያንዳንዱ ሠራተኛ ከውጭ ወደ እርባታ ጣቢያዎች የሥራ ልብሱን ለብሶ፣ ንጽህናውን ጠብቆ እንዲገባ ይደረጋል። የማምረቻ ቦታዎቻችን ለጤና አጠባበቅ ሲባል ለጎብኚዎች ክፍት አይደሉም። የግድ መግባት ያለባቸው ጎብኚዎች ከመጡ ለዚህ የተዘጋጀ ልብስ አልብሰን ነው የምናስገባው። ከዚህ አንጻር በሽታ ወደእርባታ ጣቢያዎቻችን እንዳይገባ የምናደርገው ማኔጅመንት በጣም ወሳኝ ነው፣ በጥሩ ሁኔታ እየተሠራ ያለ ነው። የእኛ ዶሮዎች ጫጩት ሆነው የምናስገባው ከአውሮፓ ነው። ዶሮ ማምጣት በምንፈልግበት ሰዓት እኛ ከምናደርገው በተጨማሪ የእንስሳትና የዓሳ ሐብት ሚኒስቴር በምናስመጣበት ሀገር የዶሮ በሽታ አለመኖሩን ሲያረጋግጥ ነው ፈቃድ የሚሰጠን። ከዚያ በኋላ የሚመጡ ዶሮዎችን ቦታ አዘጋጅተን ነው የምንጠብቃቸው። ምግባቸውን የሚሠሩ ባለሙያዎች አሉ። ጤንነታቸውን የሚጠብቁ ባለሙያዎች አሉ። የመድኃኒት፣ የክትባት ችግር የለም። ተገቢውን ያልተቋረጠ ክትትል ማድረግ የሥራችን አንዱ አካል ነው። ሌላው ቀርቶ በየዓመቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ አዳዲስ የዶሮ በሽታዎች ሊያጋጥም የሚችልበት ሁኔታ ቢፈጠር ከዚህ ተለዋዋጭ ሁኔታ ጋር አብሮ የሚሄድ የመከላከል ሥራ በየጊዜው እናከናውናለን።

ሰንደቅ፡- የእናንተ የዶሮ እርባታ ከሙያ አንጻር የሚያከናውነው ተግባር ምን ይመስላል?

ዶ/ር ዳንኤል፡- ከላይ እንደገለጽኩት የእኛ ፋርም ሥራ የሚከናወነው በተሟላ ባለሙያዎች ስለሆነ የዶሮ እርባታ ሕግና ሥርዓት ጠብቀን በአመጋገባቸው፣ በጤና ክትትላቸው እንዲሁም በማኔጅመንት ደረጃውን የጠበቀ የዶሮ ምርት ሥራ እናከናውናለን።

ሰንደቅ፡- ከገበያ ማረጋጋት አንጻር የኤልፎራ አስተዋጽኦ ዘርዘር አድርገው ቢገልጹልኝ?

አቶ አንበሴ፡-  ባለፉት ዓመታት ለበዓላት ያከናወንናቸው የዶሮ ሽያጭ ከሌሎች ገበያ ጋር ሲነፃፀር ትልቅ ልዩነት አለው። በአብዛኛው ኅብረተሰቡ ተመጣጣኝ በሆነ ዋጋ የምንሸጠውን ዶሮ እየገዛ ነው። ኅብረተሰቡን በጥሩ ሁኔታ እያገለገልን መሆኑ ትልቁ ማሳያ አንዱ ይሄ ነው። በሌላ በኩል ገበያው አስፈላጊ ባልሆነ የዋጋ ንረት ሲሯሯጥ የእኛ ኩባንያ ያንን ተከትሎ የሚሄድ አይደለም። የእኛንም ትክክለኛ የማምረቻ ወጪና፣ የኅብረተሰቡን አቅም ባመጣጠነ መልኩ ዶሮዎችን ለገበያ እናቀርባለን። ከሁሉ በላይ በጥራት በኩል በጣም የምንተማመንበት ነው። ይሄንንም በማየት ነው በተወሰኑ ቦታዎች ብቻ ይሸጥ የነበረውን ዶሮ ወደ 19 የመዳረሻ ቦታዎች እንድናሳድግ ያስገደደን። ምክንያቱም ሰው ተሰልፎ ሳያገኝ እንዳይሄድ ወይንም እኛ ጣቢያ ድረስ መጥቶ ተጉላልቶ፣ ለትራንስፖርት ተጨማሪ ገንዘብ እንዳያወጣ በአቅራቢያው ለማቅረብ በማሰብ ነው። እናም ሕዝብ በዛ ያለባቸውን አካባቢዎች ታሳቢ ያደረገ የመሸጫ ቦታዎችን ከፍተናል።

ሰንደቅ፡- የዘንድሮውን የዘመን መለወጫ በዓል በማስመልከት ኤልፎራ ዶሮዎችን ለኅብረተሰቡ ለማቅረብ ያደረገው ዝግጅት ምን ይመስላል?

አቶ አንበሴ፡-  በመጀመሪያ ደረጃ የአቅርቦት መጠኑን ጨምረናል። በሁለተኛ ደረጃ በተለያዩ ቦታዎች የኤልፎራ ዶሮ ያልሆነውን ፣የኤልፎራ ነው ብለው በሚሸጡ ግለሰቦች ኅብረተሰቡ እንዳይታለልና መልካም ስማችንን ለመጠበቅ በማሰብ ከፊት ለፊት የኤልፎራ ዓርማ (ሎጎ) ያለው፣ ከጀርባ ደግሞ የኩዊንስ የሱፐርማርኬት ዓርማ (ሎጎ) ያለው አረንጓዴ ልብስ (ጋዋን) ለሽያጭ ሠራተኞቻችን አዘጋጅተናል። በተጨማሪ ሽያጭ ሲፈፀም የኤልፎራ ሕጋዊ ደረሰኝ እየቆረጡ ስለሚሰጡ ይህን ኅብረተሰቡ እንዲያውቅ መልዕክታችንን በዚህ አጋጣሚ እናስተላልፋለን።

ይምረጡ
(2 ሰዎች መርጠዋል)
1701 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 1062 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us