ዩናይትድ አውቶ ሜንቴናስ ዘመናዊ አወቶቡሶችን ለባለሀብቶች አስረከበ

Wednesday, 29 June 2016 12:12

የሚድሮክ ኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ግሩፕ እህት ኩባንያ የሆነው ዩናይትድ አውቶ ሜንተናስ ያስመጣቸውን ዘመናዊ የህዝብ ማመላሻ አውቶብሶች ለባለሀብቶች አስረከበ። ባለፈው ሀሙስ በኩባንያው ቅጥር ጊቢ በተካሄደ የርክክብ ስነስርዓት ዘመናዊ አውቶብሶቹ ለእይታ የቀረቡ ሲሆን አውቶብሶቹን ያቀረበው የቻይናው ኪንግሎንግ ኩባንያ መሆኑ ተመልክቷል። በእለቱ በኪንግ ሎንግ ኩባንያ ተወካይ ከተደረገው ገለፃ መረዳት እንደቻልነው ኩባንያው በቻይና ካሉት ሶሰት ግዙፍ ተሸከርካሪ አምራች ኩባንያዎች መካከል አንዱ ነው። እ.ኤ.አ ከ2000 ጀምሮ የተለያዩ መኪኖችን እያመረተ ከ120 አገራት በላይ ኤክስፖርት የሚያደርግ መሆኑም ታውቋል።

 

ዘመናዊዎቹ ባለሙሉ ምቾት የህዝብ ማመላለሻ አውቶብሶቹ አገር ውስጥ ከመግባታቸው በፊት የአገሪቱን ነባራዊ ሁኔታ ታሳቢ ባደረገ መልኩ በትእዛዝ እንዲገጣጠሙ የተደረጉ ናቸው ተብሏል። ኮች ባስ በመባል የሚታወቁት ረዣዥሞቹና ቁመታሞቹ አውቶብሶች ጂፒኤስ የተገጠመላቸው፣ ኢንጂናቸው ዩሮ-3  ደረጃ የሆነና አረንጓዴ ቴክኖሎጂን ታሳቢ ያደረገ፣ በአንድ መቶ ኪሎ ሜትር ከ34 እስከ 36 ኪሎ ሜትር መጓዝ የሚችሉ፣ በአሽከርካሪዎች ያልተገባ የማሽከርከር ተግባር የሚከሰት ከሆነ የማስጠንቀቂያ መልዕክትን የሚያስተላለፉበት ቴክኖሎጂ የተገጠመላቸው ናቸው። ከዚህም በተጨማሪ ወንበሮቹ ወደ ኋላ የሚለጠጡና ወደ ቀኝና ወደ ግራም የሚሰፉ መሆናቸው ታውቋል። ቴሌቭዥንና ሬዲዮን ያካተቱ ሲሆን እያንዳንዱ ተሳፋሪም በመቀመጫው እንዳለ የአገልግሎት ጥሪ የሚያስተላልፍበት ደውልም እንዲገጠምላቸው ተደርጓል።

 

ለጊዜው አምስት አውቶብሶች አገር ውስጥ የገቡ ሲሆን በቀጣይ ሌሎች ተጨማሪ ተመሳሳይ አውቶብሶችን ለማስገባት እቅድ ተይዟል። በስነ ስርዓቱ ላይ የተገኙት የመንገዶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ካሳሁን ሀይለማርያም የአውቶብሶቹን ዘመናዊነት አድንቀው፣ ሀገሪቱ ከተያያዘቸው እድገት አኳያ የትራንስፖርት አገልግሎት ዘርፉን በተገቢው መንገድ ለማሳደግ መሰል ዘመናዊ አውቶብሶች የሚያስፈልጉ መሆኑን አስታውቀዋል። ቀደም ባሉት ጊዜያት አገሪቱ የነበረው አጠቃላይ የተሸከርካሪ ቁጥር አነስተኛ እንደነበር የጠቆሙት ኃላፊው፤ የቀደመው ሁኔታ ተቀይሮ አገር ውስጥ የሚገቡት ያገለገሉና አዳዲስ ተሽከርካሪዎች ቁጥር በአሁኑ ሰዓት በአመት ወደ አንድ መቶ ሺህ እየተጠጋ መሆኑን ገልፀዋል።

 

 የሚድሮክ ኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ቺፍ ኤግዚኪዩቲቭ ኦፊሰር ዶክተር አረጋ ይርዳው በበኩላቸው፤ ተሸከርካሪዎችን ከውጪ እንዳለ ከማስገባት ይልቅ ቀስ በቀስ አገር ውስጥ እንዲገጣጠሙ ማድረጉ የውጭ ምንዛሪን የሚቆጥብ፣ የቴክኖሎጂ ሽግግር እንዲኖር የሚያደርግና ለዜጎችም የስራ እድልን የሚፈጥር በመሆኑ ኩባንያው በቀጣይ ወደዚህ ስራ የሚገባበት ሂደት ይመቻቻል ብለዋል።  

ይምረጡ
(1 ሰው መርጠዋል)
933 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 104 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us