ዩኒቲ ዩኒቨርስቲ 15ኛውን ዓመታዊ የምርምር ኮንፍረንሱን አካሄደ

Wednesday, 29 June 2016 12:09

ዩኒቲ ዩኒቨርስቲ 15ኛውን ዓመታዊ መልቲዲሲፕለነሪ የምርምር ኮንፍረንሱን ከሰኔ16 እሰከ 18 ቀን 2008 ዓ.ም አካሂዷል። የምርምር ኮንፍረንሱ በሚድሮክ ኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ዋና መ/ቤት አዳራሽ የተካሄደ ሲሆን በተለያዩ የሙያና የትምህርት ዘርፎችም በርካታ ጥናቶች ቀርበው ውውይቶች ተካሂዶባቸዋል።

 

ከቀረቡት ጥናቶች መካከል አየር ለውጥንና ተፅዕኖውን፣ የሚመለከቱ አኒርጂና ልማትን፣ በቀርቀሀ ላይ የሚሰሩ ፈጠራዎች ለገጠሩ ልማት የሚኖራቸውን አስተዋፅዕኦ ያሳዩ፣ ይገኙበታል። ከዚህም በተጨማሪ የብሄራዊ ባንክ ህጎች በግል ንግድ ባንኮች ላይ ያላቸውን ተፅዕኖ በተመለከተም ጥናት ቀርቧል።

 

 ስነልቦናን ጨምሮ በበርካታ የሙያ ዘርፎች ላይም የተደረጉ ጥናቶች የቀረቡ ሲሆን በእያንዳንዱ ጥናት ላይም ሙያዊ አስተያየቶች እየተሰጡ ሰፋ ያሉ ውይይቶች ተካሂደዋል። ላላፉት ተከታታይ አምስት ዓመታት የትራፊክ አደጋ  በአዲስ አበባ ከተማ እያደረሰ ያለውን ጉዳትና እያስከተለ ያለውን የጤንነት፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች የሚዳስስ ጥናትም የዚሁ ኮንፍረንስ አካል ነበር።

 

 ይሄው ጥናት ከመንገድ ጋር በተያያዘ ያሉትን ችግሮች ከተሸከርካሪዎች፣ከመኪና መንገዶች፣ ከአሽከርካሪ ማሰልጠኛ ተቋማትና ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት አንፃር ፈትሿል። በከተማዋ የተሳለጠ የትራፊክ ፍሰት እንዳይኖርና አደጋዎችም የተበራከቱ እንዲሆኑ የሚያደርጉ በርካታ ምክንያቶችም ተመላክተዋል። ከእነዚህም ውስጥ የተሸከርካሪ፣ የእግረኛና የእንስሳት መንገድ የተሳለጠ አለመሆን፣የአሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ ተቋማት የብቃት አናሳነት፣ በመንጃ ፈቃድ አሰጣጥ ሂደት ያሉት ብልሹ አሰራሮችም በዋና ምክንያትነት ተጠቅሰዋል።

 

ከቀረቡት ጥናቶች መካከል የአየር ለውጡ ሂደት አነስተኛ ይዞታ ባላቸው ገበሬዎች ላይ እያደረሰ ያለውን አሉታዊ ተፅዕኖ በተመለከተ ሰፋ ያለ ዳሰሳ ያካሄደው ጥናት ይገኝበታል። አቶ አባይነህ አማረ በተባሉ ባለሙያ የቀረበው ይኸው ጥናት በአባይ ተፋሰስ ሙገር አካባቢ የሚገኝ አካባቢን ለይቶ በናሙናነት የተደረገ ጥናት ሲሆን በደጋ፣ በወይና ደጋና በቆላ አርሶ አደሮች የአየር ለውጥ ተጋላጭነት ደረጃ ላይ ሰፋ ያለ ዳሰሳን አካሂዷል።

 

 በዚሁ ጥናት ላይም ከደጋ አርሶ አደሮች ይልቅ የቆላ አርሶ አደሮች ለአየር ንብረት ለውጥ ያላቸው ተጋላጭነት ከፍተኛ መሆኑና የቆላው አካባቢ አርሶ አደሮች የአየር ለውጡን ተከትለው ራሳቸውን ከነባራዊው ሁኔታ ጋር የማጣጣም አቅማቸው (Adaptive Capacity) አነስተኛ መሆኑን ተመልክቷል። ጥናት አቅራቢው ከዚህም በተጨማሪ የቆላ አካባቢ አርሶ አደሮች ከደጋናና ወይና ደጋ አርሶ አደሮች ይልቅ ለአየር ለውጥ ያላቸው ተጋላጭት (Vulnerability) ከፍተኛ መሆኑንም ትንታኔ ተሰጥቶበታል። የቆላ አካባቢ አርሶ አደሮች በተነፃፃሪነት በቂ የሆነ መሰረተ ልማት የሌላቸው፣ በደካማ የኢኮኖሚ አቅም ላይ የሚገኙ መሆናቸውና በሌሎች መሰል ችግሮች ለአየር ንብረት  ለውጡ ተጋላጭነታቸው የሰፋ መሆኑን ከባለሙያው ጋር በነበረን ቆይታ ከሰጡን ማብራሪያ መረዳት ችለናል።

 

በአንድ ውስን አካባቢ የተደረገ ጥናት ብሄራዊ ውክልናው ምን ያህል እንደሆነ ላቀረብንላቸው ጥያቄ አቶ አባይነህ በሰጡን ምላሽ የጥናቱ አላማ በብሄራዊ ደረጃ ለሚወጡ ህጎችና ፖሊሲዎች ግብአት እንዲሆን ሳይሆን ለአንድ ውስን አካባቢ ራሱን የቻለ መፍትሄ እንደሚያስፈልግ ማሳያ ነው ብለውናል።

 

 በእለቱ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የሚድሮክ ኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ቺፍ ኤግዚኪዩቲቭ ኦፊሰር እና የዩኒቲ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር አረጋ ይርዳው ትምህርትና ምርምር የአንድ ከፍተኛ ትምህርት ተቋም የማይነጣጠሉ ተግባራት መሆናቸውን ገልፀው፤ አንደኛው ያለሌላኛው ስኬትን የማያገኝ መሆኑን አመልክተዋል። ዶክተር አረጋ በዚሁ ንግግራቸው ዩኒቲ ዩኒቨርስቲ ምርምሮችን የሚያከናውነው የጥራት ማዕከል ለመሆን ያያዘውን አላማ ለማሳካት መሆኑንም ገልፀዋል።  

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
725 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 1017 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us