ኢ/ር ዘለቀ ረዲ መጽሐፍ በቅርቡ ለንባብ ይበቃል

Wednesday, 10 May 2017 13:20

 

በኮንስትራክሽን ዘርፍ ከሚጠቀሱት ባለሃብቶች መካከል አንዱ የሆኑትና የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ የቀድሞ ከፍተኛ አመራር ኢንጂነር ዘለቀ ረዲ «የ21ኛው ክፍለ ዘመን መሳፍንቶች እና ኢትዮጵያን እንደሃገር የማስቀጠል ፈተና» በሚል ርዕስ ያዘጋጁት መጽሐፍ ከአንድ ወር በኋላ ለንባብ እንደሚበቃ ተገለጸ።

 

ኢ/ር ዘለቀ ረዲ የመጽሐፉን አጠቃላይ ይዘትና ዝግጅት አስመልክቶ በሳፋሪያን አዲስ ሆቴል ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ የመጽሐፉ ትኩረት የኢትዮጵያን ማንነት በጥልቀት የሚዳስስ ነው ብለዋል። ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር ማንናት፣ ኢትዮጵያ ድሮና ዘንድሮ ምን ዓይነት ገጽታ አላት፣ እድገቷ ምን ይመስላል፣ የኋሊት ነው ወይስ ወደፊት? የሚሉትን ርዕሰ ጉዳዮች የሚዳስስ መሆኑን ኢ/ር ዘለቀ በገለጻቸው ወቅት አስረድተዋል። መጽሐፉ በተለይ የዘመነ መሳፍንት እና የተራማጅ አስተሳስብን በማነጻጸር ኢትዮጵያ በየትኛው አስተሳሰብ ላይ ስለመሆንዋ ለመዳሰስ መሞከሩን ገልጸዋል። የዘመነ መሳፍንት አስተሳሰብ ከሀገር ጥቅም ይልቅ የግል ጥቅምን የሚያስቀድም መሆኑንና እስከዛሬ ሀገሪቷ በዚህ አስተሳሰብ የቱን ያህል ጉዳት እንደደረሰባት የሚገለጽ ሀሳብ በመፅሐፉ መስፈሩንም ተናግረዋል።

በ200 ገጾች የተሰናዳው ይኸ መጽሐፍ በሰኔ ወር ለንባብ ይበቃል ብለው እንደሚገምቱ የገለጹት ኢ/ር ዘለቀ፤ የመሸጫ ዋጋው ለጊዜው አለመወሰኑንና ከመጽሐፉ የሚገኘውን ገቢ ግን ለአንድ የበጎ አድራጎት ድርጅት ለማዋል ዕቅድ እንዳላቸው አስታውቀዋል። ኢንጂነሩ አያይዘውም በመጽሐፉ ዝግጅት ሒደት ጋዜጠኛ ዮናስ ወ/ሰንበት በአዘጋጅነት ከፍተኛ ሚና እንደነበረው የጠቀሱ ሲሆን ሌሎችም በዝግጅቱ ላይ አስተዋጽኦ የነበራቸውን ግለሰቦች በስም በመጥቀስ ምስጋና አቅርበዋል።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
15694 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 825 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us